የፈጅር አዛን ላይ አዛን ባዩ "ሐይየ ዐለል ፈላሕ" ካለ በኋላ "አስሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም" ማለቱ ከሱና ነው።

የፈጅር አዛን ላይ አዛን ባዩ "ሐይየ ዐለል ፈላሕ" ካለ በኋላ "አስሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም" ማለቱ ከሱና ነው።

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የፈጅር አዛን ላይ አዛን ባዩ "ሐይየ ዐለል ፈላሕ" ካለ በኋላ "አስሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም" ማለቱ ከሱና ነው።»

[ሶሒሕ ነው።] [Ibn Khuzaymah - Al-Bayhaqi - ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።]

الشرح

አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተናገሩት ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ካፀደቁት ሱናዎች መካከል ሙአዚኑ የፈጅር አዛን ላይ ብቻ (ሐይየ ዓለል ፈላሕ) ካለ በኋላ (አስሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም) ማለቱ ነው።

فوائد الحديث

(ከሱና ነው።) ሲል ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሱና ነው ማለቱ ነው። የዚህም ብይን ልክ ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደተናገሩት ነው።

አዛን ባዩ በፈጅር አዛን ወቅት (ሐይየ ዐለል ፈላሕ) ካለ በኋላ ሁለት ጊዜ (አስሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም) ማለቱ ይወደዳል። ይህም የፈጅር ሶላት ወቅት አብዛኛው ሰው በሚተኛበት ወቅት ስለሆነ ከእንቅልፋቸው ተነስተው ወደ ሶላት እንዲቆሙ ነው፤ ከሌሎች ሶላቶች ተነጥሎ የፈጅር ሶላት ብቻ የተለየው።

التصنيفات

አዛንና ኢቃማህ