'ቁመህ! ካልቻልክ ተቀምጠህ ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ። '

'ቁመህ! ካልቻልክ ተቀምጠህ ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ። '

ከዒምራን ቢን ሑሰይን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ኪንታሮት ነበረብኝና ስለ አሰጋገዴ ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠየቅኳቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉኝ:- 'ቁመህ! ካልቻልክ ተቀምጠህ ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ። '"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

መቆም ባልተቻለበት ወቅት ካልሆነ በቀር ለሶላት አሰጋገድ መሰረቱ መቆም እንደሆነና መቆም ካልቻለ ተቀምጦ እንደሚሰግድ ተቀምጦ መስገድም ካልቻለ በጎኑ ተጋድሞ መስገድ እንደሚችል ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ።

فوائد الحديث

በአቅም ልክ ከሁኔታ ወደ ሁኔታ መሸጋገር እንጂ አይምሮ ጤነኛ እስከሆነ ድረስ ሶላት የማትቀር ግዴታ ናት።

አንድ ሰው አምልኮን የሚፈፅመው በአቅሙ ልክ መሆኑ የኢስላምን ገርነትና ቀላልነትን ያስረዳናል።

التصنيفات

ባለ ዑዝር (ተቀባይነት ያለው ምክንያት ያላቸው ሰዎች) የሚሰግዱት አሰጋገድ