إعدادات العرض
አንዲት ሴት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተሳተፉበት አንድ ጦርነት ላይ ተገድላ ተገኘች። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ…
አንዲት ሴት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተሳተፉበት አንድ ጦርነት ላይ ተገድላ ተገኘች። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴትና ህፃናትን መግደልን አወገዙ።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: አንዲት ሴት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተሳተፉበት አንድ ጦርነት ላይ ተገድላ ተገኘች። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴትና ህፃናትን መግደልን አወገዙ።
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî മലയാളം Kiswahili සිංහල অসমীয়া ગુજરાતી Tiếng Việt دری Nederlands Soomaali नेपाली پښتو ไทย Svenska Oromoo Кыргызча Română తెలుగు Lietuvių Malagasy ಕನ್ನಡ Српски Yorùbáالشرح
በአንድ ጦርነት ወቅት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዲት ሴት መገደሏን ተመለከቱ። እርሳቸውም የሴትንና ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህፃናት መገደልን አወገዙ።فوائد الحديث
ከሴትና ከህፃናት ሆነው እንዲሁም እንደነሱ ደካሞች የሆኑ የጃጁ ሽማግሌዎችና ባህታዊዎች በስትራቴጂ እውቀታቸው ሙስሊሞችን በመዋጋት ላይ የሚያግዙ ካልሆኑ በቀር አይገደሉም። እንደዚህ ሆነው ከተገኙ ግን ይገደላሉ።
ሴቶችና ህፃናትን መግደል መከልከሉን እንረዳለን። ይህም እነዚህ አካላት ሙስሊሞችን ስለማይዋጉ ነው። በአላህ መንገድ የመታገል ዋነኛ አላማው የእውነት ጥሪ ወደ ሰዎች ባጠቃላይ እስኪደርስ ድረስ የሚያቅቡ አካላትን ሀይል መስበር ብቻ ነውና።
በዘመቻዎችና ጦርነቶች ሳይቀር የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እዝነት ምን ያህል እንደነበር እንረዳለን።
التصنيفات
የጂሃድ ስነ-ስርዓት