የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንጥላቸውን እስክመለከት ድረስ በጭራሽ ሙሉ አፋቸውን ከፍተው ሲስቁ ተመልክቻቸው አላውቅም። ሲስቁ…

የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንጥላቸውን እስክመለከት ድረስ በጭራሽ ሙሉ አፋቸውን ከፍተው ሲስቁ ተመልክቻቸው አላውቅም። ሲስቁ ፈገግ ብቻ ነበር የሚሉት

ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንጥላቸውን እስክመለከት ድረስ በጭራሽ ሙሉ አፋቸውን ከፍተው ሲስቁ ተመልክቻቸው አላውቅም። ሲስቁ ፈገግ ብቻ ነበር የሚሉት"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሳቃቸው እንጥላቸው እስኪታይ ድረስ ከመጠን ያለፈ እንዳልነበር፤ ከሳቁም ፈገግ ብቻ ይሉ እንደነበር ተናገረች። እንጥል ማለት ከጉሮሮ በላይ የተንጠለጠለ ስጋ ነው።

فوائد الحديث

የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንዳች ነገር ከተመቻቸው ወይም የተደሰቱበት ጊዜ የሚስቁት ሳቅ ፈገግታ ነበር።

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «"በሳቅ ጉዳይ በሙሉ አፋቸው ሲስቁ አላየኃቸውም" ማለት ለመሳቅ ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ ሆነው የተሟላ ሳቅ ሲስቁ ማለት ነው።»

ሳቅ ማብዛትና በመንተክተክ ድምፅን ከፍ ማድረግ የደጋጎች ባህሪ አይደለም።

ሳቅ ማብዛት ሰውዬው በወንድሞቹ መካከል ያለውን ግርማና ክብር ይቀንስበታል።

التصنيفات

የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሳቅ