ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት የገቡ ጊዜ 'አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹብሢ ወልኸባኢሥ' ይሉ ነበር።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከወንድ…

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት የገቡ ጊዜ 'አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹብሢ ወልኸባኢሥ' ይሉ ነበር።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከወንድ ሰይጣንና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት የገቡ ጊዜ 'አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹብሢ ወልኸባኢሥ' ይሉ ነበር።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከወንድ ሰይጣንና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሽንት ወይም ከሰገራ ለመፀዳዳት ወደ ስፍራው መግባት የፈለጉ ጊዜ ከወንድ ሰይጣኖችና ከሴት ሰይጣናት ክፋት በአላህ ይጠበቁና ወደርሱም ይጠጉ ነበር። በተጨማሪ "አልኹብሢ ወልኸባኢሥ" የሚለው ቃል ክፋትና ነጃሳ ተብሎም ተተርጉሟል።

فوائد الحديث

መፀዳጃ ቤት መግባት በሚፈለግ ጊዜ ይህን ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።

ሁሉም ፍጡራን በሁሉም ሁኔታዎቻቸው ላይ የሚያውካቸውን ወይም የሚጎዳቸውን ለመከላከል ወደ ጌታቸው ፈላጊዎች መሆናቸውን እንረዳለን።

التصنيفات

የመፀዳጃ ቤት ስነ-ስርዓት, የመፀዳጃ ቤት ስነ-ስርዓት