'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'

'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'

ዓኢሻህ ረዲየሏሁ ዐንሀ እንዲህ ማለቷ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ 'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'"

[ሶሒሕ ነው።] [An-Nasaa’i]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አራክ በተባለው ወይም በአምሳያው በሆነ መፋቂያ ጥርስን መፋቅ አፍን ከቆሻሻ እና ከመጥፎ ጠረን እንደሚያፀዳ ነገሩን። ይህንኑ ማድረግም ለአሏህ ታዛዥነትና ለትእዛዙ ምላሽ መስጠት ከመሆኑ ባሻገር አሏህ የሚወደውን ንፅህናንም የሚያስተርፍ ስለሆነ ድርጊቱ የአሏህን ውዴታ ማግኛ ሰበብ መሆኑን ነገሩን።

فوائد الحديث

ጥርስን መፋቅ ያለውን ትሩፋትና ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ዑመታቸው ድርጊቱን ያበዛ ዘንድ ማነሳሳታቸውን እንረዳለን።

ቢፍቁበት የተሻለው "አራክ" የተባለውን የዛፍ ግንድ (መፋቂያ) ከመሆኑም ጋር በምትኩ የጥርስ ብሩሽ ከሳሙናው ጋር መጠቀምም ይቻላል።

التصنيفات

ተፈጥሯዊ ሱናዎች