إعدادات العرض
ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።
ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።
ከተሚም አድዳሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።" እኛም "ለማን ነው (የምንቆረቆረው)" አልናቸው። እሳቸውም "ለአላህ፣ ለመጽሐፉ፣ ለመልክተኛው፣ ለሙስሊሞች መሪዎችና ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ።" አሉ።
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල தமிழ் ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek Moore नेपाली Oromoo Wolof Soomaali Български Українська Azərbaycan bm ქართული lnالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የኢስላም ሃይማኖት በኢኽላስና በእውነተኝነት ላይ የቆመ መሆኑን ተናገሩ። ይህም ሁሉም አማኝ የታዘዘውን አላህ ግዴታ ባደረገው መልኩ ምንም ሳያጓድልና ሳያታልል በተሟላ መልኩ እስኪፈፅም ድረስ ነው ቅን እንዲሆን የታዘዘው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "ለማን ነው ተቆርቋሪነቱ?" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም እንዲህ አሉ፦ በመጀመሪያ: ጥራት ለተገባውና ከፍ ላለው አላህ ተቆርቋሪ (ታማኝ) መሆን ነው። ይህም፦ ለሱ የምንሰራውን ስራ በማጥራትና ባለማጋራት፣ በጌትነቱ፣ በተመላኪነቱ፣ በስሞቹና በባህሪያቶቹ በማመን፣ ትእዛዞቹን በማላቅና በሱ ወደማመን ሌሎችን በመጣራት ነው። ሁለተኛ: ለመጽሐፉ ተቆርቋሪ (ታማኝ) መሆን ነው። እሱም የተከበረው ቁርአን ነው። ይህም: ቁርአን የአላህ ቃል መሆኑንና የመጨረሻው መጽሐፉ መሆኑን በማመን፣ ከእሱ በፊት የነበሩትን ሁሉ ድንጋጌዎች የሻረ መሆኑን በማመን፣ እሱን በማላቅ፣ ትክክለኛ በሆነ መልኩ በማንበብ፣ ግልፅ የሆኑትን በመተግበር አሻሚ የሆኑትን በማመን፣ ከአጥማሚዎች ትርጓሜም በመከላከል፣ በተግሳፆቹ በመመከር፣ ውስጡ ያሉትን እውቀቶች በማሰራጨትና ወደርሱ በመጣራት ነው። ሶስተኛ: ለመልክተኛው ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን ነው። ይህም: እሳቸው ከመልክተኞች የመጨረሻ መሆናቸውን በማመን፣ ከሳቸው የመጣውን ሁሉ እውነትነቱን በመቀበል፣ ትእዛዛቸውን በመፈፀም፣ ክልከላቸውን በመራቅ፣ እሳቸው ባመጡት ድንጋጌ ካልሆነ በቀር አላህን ባለማምለክ፣ ሐቃቸውን በማላቅና በማክበር፣ ጥሪያቸውን በማሰራጨት፣ ሸሪዐቸውን በማስፋፋት፣ እሳቸው ላይ የሚቀርቡ ክሶችን ውድቅ በማድረግ ነው። አራተኛ: ለሙስሊም መሪዎች ቅን ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን ነው። ይህም: በሀቅ ላይ በመተባበር፣ ጉዳያቸውን ባለመጋፋትና በአላህ ትእዛዛቶች ሲያዙን እነሱን ሰምቶ በመታዘዝ ነው ። አምስተኛ: ለሙስሊሞች ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን ነው። ይህም: ለነሱ በጎ በማድረግ፣ እነሱን ወደ በጎ በመጣራት፣ እነሱ ላይ ጉዳት ከማድረስ በመቆጠብ፣ ለነሱ መልካምን በመውደድ፣ በበጎና አላህን በመፍራት ላይ ከነርሱ ጋር በመተባበር ነው።فوائد الحديث
ለሁሉም ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን መታዘዙ፤
በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ የተቆርቋሪነት (ቅን/ ታማኝ) ደረጃ የላቀ መሆኑን፤
የእስልምና ሃይማኖት እምነቶችን፣ ንግግሮችንና ተግባራቶችን ያጠቀለለ መሆኑን፤
ከነሲሓ መካከል አንዱ ቅንነቱ ለተገባው አካል ከማታለል ነፍሳችንን ማፅዳትና ለሱ መልካምን መፈለግ ነው።
መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድን ነገር በጥቅሉ አውስተው ከዚያም መዘርዘራቸው የሳቸውን የማስተማር ብቃታቸው ውበትን ይጠቁማል።
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለአላህ ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) በመሆን ጀምረው ከዚያም ለመጽሐፉ ከዚያም ለመልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዚያም ለሙስሊም መሪዎች ከዚያም ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) በመሆን ማጠቃለላቸው የትኛውንም ነገር እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ጉዳይ ሊጀመር እንደሚገባው እንረዳለን።
التصنيفات
መሪ በህዝብ ላይ ያሉት መብቶች