إعدادات العرض
ዒድን ከዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጋር ለመስገድ ተገኘሁ። እንዲህም አሉ: "እነዚህ ሁለት ቀናቶች የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ…
ዒድን ከዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጋር ለመስገድ ተገኘሁ። እንዲህም አሉ: "እነዚህ ሁለት ቀናቶች የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመጾም የከለከሉት ቀናቶች ናቸው። (እነርሱም) ከጾማችሁ የምትፈቱበት ቀን (ዒድ አልፊጥር) እና ሌላኛው ቀን ደግሞ ከእርዳችሁ የምትበሉበት የሆነው ቀን (ዒደል አድሓ) ናቸው።
ኢብኑ አዝሃር ነፃ ያወጡት ባሪያ ከሆነው ከአቡ ዑበይድ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዒድን ከዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጋር ለመስገድ ተገኘሁ። እንዲህም አሉ: "እነዚህ ሁለት ቀናቶች የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመጾም የከለከሉት ቀናቶች ናቸው። (እነርሱም) ከጾማችሁ የምትፈቱበት ቀን (ዒድ አልፊጥር) እና ሌላኛው ቀን ደግሞ ከእርዳችሁ የምትበሉበት የሆነው ቀን (ዒደል አድሓ) ናቸው።"»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî සිංහල Kiswahili Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી Nederlands മലയാളം ไทย Românăالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዒደል ፊጥርና ዒደል አድሓን ከመጾም ከለከሉ። ዒደል ፊጥር ከረመዳን ወር ጾም የሚፈታበት ቀን ስለሆነ ነው። የዒደል አድሓ ቀን ደግሞ ከኡድሒያው ስጋ የሚበላበት ቀን ስለሆነ ነው።فوائد الحديث
የዒደል ፊጥርና አድሓ ቀናትን መጾም ክልክል ነው። እንዲሁም የአያመ ተሽሪቅ ቀናትም ዒደል አድሓን ተከትለው የሚመጡ ቀናት ስለሆኑ ሐጅ ላይ ሆኖ የሚያርደውን ያላገኘ ሰው እስካልሆነ ድረስ መጾም ክልክል ነው። ሐጅ ላይ የሚያርደው ያጣ ግን ለርሱ አያመ ተሽሪቆችን መጾም ይፈቀድለታል።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ሁለቱ ቀናት ባህሪያቸውን ገልፆ የመከልከሉ አስፈላጊነት ማፍጠር ግዴታ የሆነበትን ምክንያት ለመጠቆም ነው ተብሏል። እርሱም በዒደል ፊጥር ከጾም መለያየታችንንና ከዚህ ቀን በኋላ ያለውን ቀን በመብላት ጾሙ መሙላቱን ለማሳየት ሲሆን ዒደል አድሓ ደግሞ በማረድ ቁርባን ያቀረበ ሰው ካረደው እንዲበላ ነው።»
ኹጥባ አድራጊ ሰው በኹጥባው ወቅት ከጊዜው ጋር ተያያዥ የሆኑን ህግጋት ማውሳትና አጋጣሚዎችን ማጥናቱ ይወደድለታል።
ከኡዱሒያ እርድ መብላት በሸሪዓ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
التصنيفات
በፆመኛ ላይ ክልክል የሆኑ ነገሮች