ፍፁም ወዳጄ የሆኑት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ነገሮች ላይ አደራ ብለውኛል። ከሁሉም ወር ሶስት ቀናት በመጾምን፣ የዱሓን…

ፍፁም ወዳጄ የሆኑት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ነገሮች ላይ አደራ ብለውኛል። ከሁሉም ወር ሶስት ቀናት በመጾምን፣ የዱሓን ሁለት ረከዓ በመስገድንና ከመተኛቴ በፊት ዊትር መስገድን አደራ ብለውኛል።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ፍፁም ወዳጄ የሆኑት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ነገሮች ላይ አደራ ብለውኛል። ከሁሉም ወር ሶስት ቀናት በመጾምን፣ የዱሓን ሁለት ረከዓ በመስገድንና ከመተኛቴ በፊት ዊትር መስገድን አደራ ብለውኛል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ተወዳጁና ባልደረባው የሆኑት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሶስት ነገሮች አደራ እንዳሏቸውና ቃልኪዳንም እንዳስገቧቸው ተናገሩ: የመጀመሪያው: ከሁሉም ወር ሶስት ቀናትን መጾም ነው። ሁለተኛው: በየቀኑ ሁለት ረከዓ ዱሓ መስገድ ነው። ሶስተኛው: ከመተኛት በፊት ዊትር መስገድ ነው። ይህ ግን የሌሊቱ መጨረሻ ላይ አልነቃም ብሎ ለፈራ ነው።

فوائد الحديث

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሶሐቦቻቸው የሚመክሩት ምክር የሚለያየው ስለባልደረቦቻቸው ሁኔታ ባላቸው እውቀት ላይና ለእያንዳንዱ ሁሉ የሚስማማውን በማወቃቸው ላይ የተመሰረተ ነው። ጠንካራው ጂሃድ ይስማማዋል፤ አምላኪው አምልኮ ይስማማዋል፤ አዋቂው እውቀት ይስማማዋል፤ ልክ እንደዚሁ ሌሎቹንም እንደሚስማማቸው ይመክሯቸዋል።

ኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒ እንዲህ ብለዋል: "በየሁሉም ወር ሶስት ቀን መጾም ሲሉ በግልፅ የሚፈለገው ጨረቃ የምትደምቅባቸው ቀኖችን ነው። እነሱም በሂጅሪያ አቆጣጠር የወሩ አስራ ሶስተኛ፣ አስራ አራተኛና አስራ አምስተኛ ቀኖች ናቸው።"

ኢብኑ ሐጀር አልዓስቀላኒ እንዲህ ብለዋል: "እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ዊትርን ከእንቅልፍ ማስቀደም እንደሚወደድ እንረዳለን። ይህ ግን መንቃቱን ላልተማመነ ሰው ነው።"

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በርካታ ባልደረቦቻቸውን በነርሱ ማዘዛቸው የነዚህን ሶስት ስራዎች አንገብጋቢነት ያስረዳናል።

ኢብኑ ደቂቅ አልዒድ (የዱሓ ሁለት ረከዓ) በሚለው ንግግር ዙሪያ እንዲህ ብለዋል: "ምናልባት ቢያንስ መሰራት ያለበትን መጥቀሳቸው ይሆናል። በዚህም የዱሓ ሶላት ተወዳጅ መሆኑንና ትንሹም ሁለት ረከዓ መሆኑን ያስረዳናል።"

የዱሓ ሶላት ወቅት: ፀሐይ ከወጣች ከአስራ አምስት ደቂቃ በኋላ አካባቢ ይጀምርና እስከ ዙህር አስር ደቂቃ አካባቢ እስኪቀረው ነው። ቁጥሩም: ትንሹ ሁለት ረከዓ ነው። ብዙውስ በሚለው በዑለሞች መካከል የሃሳብ ልዩነት አለ። ስምንት ረከዓም ተብሏል። ገደብ የለውምም ተብሏል።

የዊትር ወቅት: ከዒሻ ሶላት በኋላ ጎህ እስኪወጣ ድረስ ነው። ትንሹ አንድ ረከዓ ነው። ብዙው አስራ አንድ ረከዓ ነው።

التصنيفات

የፈቃደኝነት ጾም