إعدادات العرض
'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች።
'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች። ይህም አንዳቸው ዉዱእ ሲያደርግ ዉዱእን አሳምሮ ከዚያም ከሶላት በስተቀር ሳያንቀሳቅሰው ከሶላትም በስተቀር ሌላን ሳይፈልግ ወደ መስጅድ ከመጣ መስጂድ እስኪገባ ድረስ በሚራመደው እያንዳንዱ እርምጃ ልክ ለርሱ ደረጃው ከፍ ይደረግለታል፤ ወንጀሉም ከርሱ ላይ በሷው ይራገፍለታል። መስጂድ የገባ ገዜም በሶላቷ ምክንያት እስከተጠመደ ድረስ ሶላት ውስጥ ነው። አንዳችሁ በሰገደበት ስፍራ ላይ እስከዘወተረ ድረስም ሰዎችን እስካላወከና ዉዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላእክቶች በርሱ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ። 'አላህ ሆይ እዘንለት፣ አላህ ሆይ ማረው፣ አላህ ሆይ ፀፀቱን ተቀበለው' ይላሉም።'"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands తెలుగు മലയാളം ไทย Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuvių Shqip Wolof Українська ქართული Moore Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሙስሊም በህብረት የሰገደ ጊዜ ይህቺ ሶላቱ ቤቱ ውስጥ ወይም ሱቁ ውስጥ ከሚሰግደው ሰላት ሀያ ምናምን እጥፍ የምትበልጥ መሆኗን ተናገሩ። ቀጥለውም የዚህን ምክንያት ተናገሩ። እርሱም ሰዉዬው ዉዱእን አሟልቶና አሳምሮ አድርጎ ከዚያም ሶላትን ብቻ ፈልጎ ወደ መስጊድ እስከወጣ ድረስ በእያንዳንዷ እርምጃው ምክንያት ደረጃው ከፍ ይላል፤ ወንጀሉም ይታበስለታል። መስጂድ ገብቶም ሶላትን እየጠበቀ ከተቀመጠ ሶላትን እስከተጠባበቀበት ጊዜ ድረስ የሶላትን ምንዳና አጅር ያገኛል። መላእክቶችም የሰገደበት ስፍራ ላይ እስከተቀመጠ ድረስ ለርሱ እንዲህ እያሉ ዱዓ ያደርጉለታል፦ "አላህ ሆይ ማረው፣ አላህ ሆይ እዘንለት፣ አላህ ሆይ ፀፀቱን ተቀበለው" ይህ ግን ዉዱኡን እስካላበላሸ ወይም ሰዎችን ወይም መላእክትን የሚያውክ ነገር እስካልፈፀመ ድረስ ነው።فوائد الحديث
ቤት ውስጥ ወይም ሱቅ ውስጥ ለብቻ የሚሰገድ ሶላት ትክክል ቢሆንም ነገር ግን ያለ በቂ ምክንያት በጀማዓ መስገድን በመተዉ ወንጀለኛ ይሆናል።
በመስጂድ ውስጥ የሚሰገድ የጀማዓ ሶላት ለብቻ ከሚሰገድ ሶላት በሀያ አምስት ወይም በሀያ ስድስት ወይም በሀያ ሰባት ደረጃ ይበልጣል።
ለአማኞች ዱዓ ማድረግ ከመላእክት የስራ ድርሻዎች መካከል አንዱ ነው።
ዉዱእ አድርጎ መስጂድ መሄድ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
التصنيفات
የጀማዓህ ሶላት ትሩፋትና ህግጋት