إعدادات العرض
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከራ ወቅት ከምትጮህ፣ ከምትላጭና ልብሷን ከምትቀዳድድ ራሳቸውን አጥርተዋል።
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከራ ወቅት ከምትጮህ፣ ከምትላጭና ልብሷን ከምትቀዳድድ ራሳቸውን አጥርተዋል።
ከአቢ ቡርዳህ ቢን አቢ ሙሳ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አቡ ሙሳ ከባድ ህመምን ታመመና ራሱን ሳተ። ጭንቅላቱ ሚስቱ ታፋ ላይ ነበር። (ስታለቅስና ስትገጥም) በርሷ ላይ አንዳችም መልስ መስጠት አልቻለም ነበር። የነቃ ጊዜ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ራሳቸውን ካጠሩት ሰው እኔም የጠራሁ ነኝ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከራ ወቅት ከምትጮህ፣ ከምትላጭና ልብሷን ከምትቀዳድድ ራሳቸውን አጥርተዋል።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî සිංහල Kiswahili Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી Nederlandsالشرح
አቡቡርዳህ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አባቱ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከባድ በሽታ እንደታመመና ራሱን እንደሳተ ተናገረ። ጭንቅላቱም ባለቤቱ ታፋ ላይ ነበር። እርሷም እየጮኸች ሙሾ አወረደች። ራሱን ስቶ ስለነበረ አንዳችም ሊመልስላት አልቻለም ነበር። የነቃም ጊዜ እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ራሳቸውን ካጠሩት ሁሉ እኔም አጥርቻለሁ። ነቢዩ: (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከነዚህ ራሳቸውን አጥርተዋል: ከ "ሷሊቃህ": በመከራ ወቅት ድምጿን ከፍ ከምታደርግ፤ ከ "ሓሊቃህ": በመከራ ወቅት ፀጉሯን ከምትላጭ፤ ከ "ሻቃህ": በመከራ ወቅት ልብሷን ከምትቀዳድ የጠራሁ ነኝ ብለዋል። እነዚህ ነገሮች የድንቁርናው ዘመን መገለጫ ስለሆኑ ነው። ይልቁንም በመከራ ወቅት ትእግስት በማድረግና ምንዳውን አላህ ዘንድ በማሰብ አዘዙ።فوائد الحديث
መከራ በሚከሰት ወቅት ልብስን ከመቅደድ፣ ፀጉርን ከመላጨትና ከመጮህ መከልከሉንና ይህም ከትላልቅ ወንጀሎች መሆኑን እንረዳለን።
ሙሾ ማውረድና መጮህ የሌለበት ማልቀስና ማዘን ክልክል አይደለም። ይህም በአላህ ውሳኔ ላይ ከመታገስ ጋር አይጋጭም። እንደውም ይህ የሚያሳየው ሃዘኔታን ነው።
አሳማሚ የሆኑ የአላህ ውሳኔዎችን በንግግርም ይሁን በድርጊት ማማረር ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
መከራ በሚከሰት ወቅት ትእግስት ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።