ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ ሰው ከኛ ገለል ይበል ወይም ከመስጂዳችን ገለል ይበል። ቤቱም ይቀመጥ" አሉ።

ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ ሰው ከኛ ገለል ይበል ወይም ከመስጂዳችን ገለል ይበል። ቤቱም ይቀመጥ" አሉ።

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: «"ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ ሰው ከኛ ገለል ይበል ወይም ከመስጂዳችን ገለል ይበል። ቤቱም ይቀመጥ" አሉ። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አረንጓዴ አታክልት ያለበት ድስት መጣላቸው። ውስጡም የሆነ ጠረን ሸተታቸው። ሲጠይቁም ውስጡ ስላለው ቡቃያ ተነገራቸው። እርሳቸውም ከርሳቸው ጋር ወደነበረ አንድ ባልደረባቸው "አስጠጉት" አሉ። እሳቸው መብላቱን እንደጠሉ ሰውየው መመልከቱን ባስተዋሉ ጊዜ እርሳቸውም "ብላ እኔ አንተ የማታወራው ጋር ስለማወራ ነው።" አሉት።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ ሰው የጀማዓ ሶላት የሚገኙ ወንድሞቹን በጠረኑ እንዳያውክ መስጂድ ከመምጣት ከለከሉት። ይህ መስጂድ ከመምጣት የመጣው ክልከላ ግን የውግዘት ክልከላ ነው። መብላቱ የሚፈቀድ ምግብ ስለሆነ ክልከላው ከመብላት አይደለም። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አረንጓዴ አትክልት ያለበት ድስት መጣላቸው። ከድስቱ ውስጥም ጠረንን ባሸተቱ ጊዜና ውስጡ ያለው ነገር ምንነቱ ሲነገራቸው ከመብላት ተቆጥበው አንዱ ባልደረባቸው እንዲበላ አቀረቡለት። ሰውዬውም እርሳቸውን ተከትሎ መብላቱን ጠላ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰውዬውን የተመለከቱት ጊዜ እንዲህ አሉት: "ብላ! እኔ ያልበላሁት በራእይ ከመላእክት ጋር ስለምንሾካሾክ ነው።" ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሰው ልጆች በመጥፎ ሽታ እንደሚታወኩት መላእክትም ይታወካሉ በማለት ተናገሩ።

فوائد الحديث

ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት ወይም ባሮ የበላ ሰው መስጂድ ከመምጣት መከልከሉን እንረዳለን።

እንደ ሲጃራ ጭስ፣ ትምባሆና የመሳሰሉት ሰጋጆች የሚታወኩበት መጥፎ ሽታ ያለው ሁሉ በፍርድ ወደነዚህ ነገሮች ይጠጋሉ።

የመከልከሉ ምክንያት ሽታ ነው። ስለዚህ አብዝቶ በመቀቀል ወይም በሌላ መንገድ ሽታው ቢወገድ መጠላቱም አብሮ ይወገዳል።

መስጂድ ውስጥ የጀመዓ ሶላት ስለሚያስመልጠው መስጂድ ውስጥ ጀመዓ ሶላት መስገድ ባለበት ሰው ላይ እነዚህ ነገሮችን መብላቱ ይጠላል። መስጂድ የመገኘት ግዴታው እንዲነሳለት ብሎ ለዘዴ መብላቱ ግን ይከለከላል።

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነጭ ሽንኩርትና የመሳሰሉትን ከመብላት የተቆጠቡት ክልክል ስለሆነ ሳይሆን ጂብሪልን (ዐለይሂ ሰላም) ስለሚያወሩ ነው።

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ብይንን ከምክንያቱ ጋር አቆራኝተው መናገራቸው የርሳቸውን የማስተማር ውበት ያሳየናል። ይህም የሚያናግሩት ሰው የመከልከል ጥበቡን በማወቅ ልቡ እንዲረጋጋ ነው።

ቃዲ እንዲህ ብለዋል: «ዑለማዎች ይህን ሐዲሥ በመመርኮዝ ከመስጂድ ውጪ ያሉ የሶላት መሰብሰቢያዎችን እንደ ዒድና ጀናዛ ሶላት ለመስገድ የሚሰበሰቡበትን አይነቱ፣ የአምልኮ መሰብሰቢያ፣ ልክ እንደዚሁ የእውቀት፣ የዚክር፣ የሰርግ ድግስና የመሳሰሉት መሰብሰቢያዎችን መስጂድ ውስጥ ከሚሰገዱት ጋር በዚሁ ፍርድ አመሳስለዋቸዋል። ሱቅና የመሳሰሉት ግን የዚህ ሐዲሥ መልእክት ውስጥ አይገቡም።»

ዑለማዎች እንዲህ ብለዋል: እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ነጭ ሽንኩርትና የመሳሰሉትን የበላ ሰው መስጂዱ ባዶ እንኳ ቢሆን መስጂድ ውስጥ ከመግባት መከልከሉን ይጠቁመናል። ይህም መላእክቶች የሚኖሩበት ስለሆነና የሐዲሡ ጥቅል ሀሳብ ይህንን ስለሚጠቁም ነው።

التصنيفات

የጀማዓህ ሶላት ትሩፋትና ህግጋት