إعدادات العرض
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ…
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ
ከአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ" ይሉ ነበር።» ትርጉሙም "ጌታችን ሆይ! ከምስጋና ጋር ጥራት የተገባህ ነህ! አላህ ሆይ! ማረኝ።" ማለት ነው።
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî සිංහල Русский Kiswahili অসমীয়া Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands മലയാളം Română ไทยالشرح
የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተናገረችው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} የሚለው ምዕራፍ የወረደላቸው ጊዜ ቁርአኑን ወደ ተግባር ለመለወጥ {ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው! ምህረትንም ለምነው።} የሚለውን የአላህን ትእዛዝ ፈጥነው ለመፈፀም በሶላት መሀል በሩኩዓቸውና በሱጁዳቸው ወቅት እንዲህ ማለትን ያበዙ ነበር፡ "ሱብሓነከ" ለአንተ ከማይመጥን ከሁሉም ጉድለት አንተን አጠራኸለሁ። "አልላሁምመ ረበና ወቢሐምዲክ" ዛትህ፣ ባህሪህና ድርጊትህ ምሉዕ ስለሆነ ምስጉን በሆኑ ውዳሴዎች አወድስሃለሁ። "አልላሁምመግፊርሊ" ከኔ ላይ ወንጀሌን አብስ! ይቅር በለኝ።فوائد الحديث
በሩኩዕና በሱጁድ ወቅት ይህን ዱዓ ማብዛት እንደሚወደድ እንረዳለን።
በእድሜ መጨረሻ ወቅት ምህረት መጠየቅ እንደሚገባ እንረዳለን። ልክ እንደዚሁ አምልኮ ውስጥ የተከሰቱ ጉድለቶች እንዲሟሉም አምልኮዎችን (በተለይም ሶላትን) ምህረትን በመጠየቅ እንድናጠናቅቅ ያስገነዝባል።
ዱዓ ተቀባይነት እንዲያገኝ ወደ አላህ ከምንቃረብባቸው ነገሮች መካከል ያማረው መመስገኛዎቹን ማውሳትና እርሱን ከጉድለቶችና ነውሮች የጠራና የፀዳ መሆኑን ማውሳት ነው።
አላህን ምህረት መጠየቅ ያለው ትሩፋትና በሁሉም ሁኔታዎች ተፈላጊ መሆኑን እንረዳለን።
የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አምልኮ የተሟላ መሆኑንና የአላህንም ትእዛዝ በተሟላ መልኩ መተግበራቸውን እንረዳለን።
التصنيفات
የሶላት አዝካሮች