إعدادات العرض
በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።
በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።"»
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Nederlands অসমীয়া Tiếng Việt Kiswahili ગુજરાતી پښتو Oromoo ไทย Românăالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ ያለውን ደረጃና እርሱ ለተቀባይነት የተገባና የማይመለስ ስለሆነ በዚህ ወቅት አላህን እንድንማፀን ገለፁ።فوائد الحديث
ይህ ወቅት ዱዓ ለማድረግ ያለውን በላጭነት እንረዳለን።
አንድ ዱዓ አድራጊ የዱዓን ስነስርዓቶች ካሟላ፣ ዱዓ ለማድረግ በላጩን ወቅትናና ስፍራ ካለመ፣ አላህን ከማመፅ ከራቀ፣ ነፍሱ አምታታችና አጠራጣሪ ነገር ውስጥ እንዳትገባ ከተጠነቀቀ፣ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ካሳመረ በአላህ ፈቃድ ዱዓው ተቀባይነት ለማግኘት የተገባ ነው።
ስለዱዓ ተቀባይነት ማግኘት መናዊ እንዲህ ብለዋል: «ማለትም የዱዓ መስፈርቶችን፣ ማዕዘናቶችንና ስነስርዓቶች ካሟላ በኋላ ከለመነው እንጂ ያጓደለው ነገር ካለ በመስተጓጎሉ ከነፍሱ በቀር ማንንም አይውቀስ።»
የዱዓ ተቀባይነት ማግኘት: ወይ የለመነው በፍጥነት ትገኝለታለች ወይም በለመነው አምሳያ ጉዳት ዞር ይደረግለታል ወይም በመጪው አለም ለርሱ ድልብ ይደረግለታል። ይህም እንደአላህ ጥበብና እዝነት የሚወሰን ነው።