إعدادات العرض
የጋብቻን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ! ጋብቻ አይንን ሰባሪና ብልትን ጠባቂ ነውና። ጋብቻን ያልቻለ ሰው መፆም አለበት። ፆም ለርሱ ማኮላሺያ (የጾታዊ ፍላጎቱን የሚቆርጥለት) ነውና።
የጋብቻን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ! ጋብቻ አይንን ሰባሪና ብልትን ጠባቂ ነውና። ጋብቻን ያልቻለ ሰው መፆም አለበት። ፆም ለርሱ ማኮላሺያ (የጾታዊ ፍላጎቱን የሚቆርጥለት) ነውና።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ሳለን እንዲህ አሉ: "የጋብቻን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ! ጋብቻ አይንን ሰባሪና ብልትን ጠባቂ ነውና። ጋብቻን ያልቻለ ሰው መፆም አለበት። ፆም ለርሱ ማኮላሺያ (የጾታዊ ፍላጎቱን የሚቆርጥለት) ነውና።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî සිංහල অসমীয়া Kiswahili Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands پښتو नेपाली മലയാളം ไทย Svenska Кыргызча Română Malagasy ಕನ್ನಡ Српски తెలుగు ქართული Mooreالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ግንኙነትንና የጋባቻን ጣጣ የቻለን ሰው እንዲያገባ አነሳሱ። ይህም ጋብቻ አይንን ከሐራም ጠባቂና ብልቱንም እጅግ በጣም ጠብቆለት ዝሙት ላይ ከመውደቅ ስለሚከለክለው ነው። የጋብቻን ጣጣ ሳይችል ግንኙነትን የቻለ ሰውም መጾም ይገባዋል። ፆም የብልትን ስሜት እና መጥፎ የዘር ፈሳሽን ይቆርጣልና።فوائد الحديث
እስልምና በጨዋነት ምክንያቶች ላይና ከዝሙት መፅዳት ላይ ጥረት ማድረጉን እንረዳለን።
የጋብቻን ጣጣ ያልቻለ ሰው በመፆም መነሳሳቱን እንረዳለን። ፆም ስሜትን ያዳክማልና።
ፆም ከመኮላሸት ጋር የተመሳሰለው: መኮላሸት ማለት የሁለቱን ፍሬዎች ደምስር መቀጥቀጥ ማለት ነው። ሁለቱ ፍሬዎች በመወገዳቸውም የግንኙነት ፍላጎት ይወገዳል። ልክ እንደዚሁ ፆምም የግንኙነትን ስሜት ያደክማል።