'ልታሟሉት ከሚገቡ መስፈርቶች ሁሉ ልታሟሉት እጅግ የተገባው ብልትን ሐላል ያደረጋቹበትን መስፈርት ነው።'

'ልታሟሉት ከሚገቡ መስፈርቶች ሁሉ ልታሟሉት እጅግ የተገባው ብልትን ሐላል ያደረጋቹበትን መስፈርት ነው።'

ከዑቅበህ ቢን ዓሚር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: 'ልታሟሉት ከሚገቡ መስፈርቶች ሁሉ ልታሟሉት እጅግ የተገባው ብልትን ሐላል ያደረጋቹበትን መስፈርት ነው።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መሙላቱ እጅግ የተገባው መስፈርት በሴት መጠቀምን ሐላል ለማድረግ ሰበብ የሆነውን መስፈርት መሆኑን እየነገሩን ነው። ይህም ሚስት በጋብቻው ውል ወቅት የምታስቀምጣቸው የተፈቀዱ መስፈርቶች ናቸው።

فوائد الحديث

ሐላልን ሐራም ሐራምን ሐላል ከሚያደርጉ መስፈርቶች በስተቀር ከሁለቱ ጥንዶች መካከል አንዱ ለሌላው ቃል የገባውን መስፈርቶች መሙላት ግዴታ ነው።

የኒካሕን መስፈርቶች ማሟላት ከሌላ መስፈርቶች የበለጠ ሊሟላ የሚገባው ነው። ምክንያቱም እነዚህ መስፈርቶች ብልትን ሐላል ለማድረግ የሚገቡት ቃል ነውና።

ኢስላም የጋብቻ መስፈርቶችን እንዲጠበቁ አፅንኦት መስጠቱ ጋብቻ በኢስላም ውስጥ ያለው ደረጃ ከፍ ያለ መሆኑን ያስረዳል።

التصنيفات

የጋብቻ መስፈርቶች