ሞቱ ያልቀረበን በሽተኛ የጠየቀና እርሱ ዘንድ ሰባት ጊዜ "አስአሉሏሀል ዐዚም ረበል ዐርሺል ዐዚም አንየሽፊከ" ካለ አላህ ከዛ ካመመው በሽታ ያድነዋል።" ትርጉሙም "ታላቁ አላህን የታላቁን…

ሞቱ ያልቀረበን በሽተኛ የጠየቀና እርሱ ዘንድ ሰባት ጊዜ "አስአሉሏሀል ዐዚም ረበል ዐርሺል ዐዚም አንየሽፊከ" ካለ አላህ ከዛ ካመመው በሽታ ያድነዋል።" ትርጉሙም "ታላቁ አላህን የታላቁን ዐርሽ ጌታ እንዲፈውስህ እጠይቃለሁ።" ማለት ነው።

ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሞቱ ያልቀረበን በሽተኛ የጠየቀና እርሱ ዘንድ ሰባት ጊዜ "አስአሉሏሀል ዐዚም ረበል ዐርሺል ዐዚም አንየሽፊከ" ካለ አላህ ከዛ ካመመው በሽታ ያድነዋል።" ትርጉሙም "ታላቁ አላህን የታላቁን ዐርሽ ጌታ እንዲፈውስህ እጠይቃለሁ።" ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድም ሙስሊም የሞቱ ወቅት ያልቀረበበትን ሙስሊም በሽተኛ ሲጎበኝ: (ታላቁን አላህ እጠይቀዋለሁ።) በዛቱ፣ በባህሪያቱና በድርጊቶቹ (የታላቁን ዐርሽ ጌታ እንዲፈውስህ) እያለ ሰባት ጊዜ ዱዓ ካደረገለት አላህ ከዛ በሽታ ይፈውሰዋል በማለት ተናገሩ።

فوائد الحديث

ለበሽተኛ ይህን ዱዓ ማለትና ሰባት ጊዜ መደጋገም እንደሚወደድ እንረዳለን።

ይህ ዱዓ እርሱ ዘንድ የተባለበት በሽተኛ በእውነተኛና በትክክለኛ አላማ እስከተባለለት ድረስ ፈውሱ በአላህ ፈቃድ እንደሚረጋገጥለት እንረዳለን።

ይህን ዱዓ በዝግታም ሆነ ድምፅን ከፍ አድርጎ ማለት ይፈቀዳል። ነገር ግን በሽተኛው እየሰማ ማለት ውስጡ ደስታን ስለሚከት (ስለሚፈጥር) በላጩና የተሻለው ነው።

التصنيفات

ሸሪዓዊ ሩቃ