የማለ ሰው በመሀላውም 'በላትና ዑዛ እምላለሁ' ያለ ሰው 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ይበል። ለባልደረባው 'ና ቁማር እንጫወት' ያለ ሰውም ይመፅውት።

የማለ ሰው በመሀላውም 'በላትና ዑዛ እምላለሁ' ያለ ሰው 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ይበል። ለባልደረባው 'ና ቁማር እንጫወት' ያለ ሰውም ይመፅውት።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የማለ ሰው በመሀላውም 'በላትና ዑዛ እምላለሁ' ያለ ሰው 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ይበል። ለባልደረባው 'ና ቁማር እንጫወት' ያለ ሰውም ይመፅውት።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ ውጪ ከመማል አስጠነቀቁ። አማኝ የሆነ ሰው ከአላህ በቀር በማንም አይምልምና። ከአላህ ውጪ የማለና ለምሳሌ በላት፣ በዑዛ የማለ ሰው (እነዚህ ሁለቱ ከእስልምና በፊት በድንቁርና ዘመን ይመለኩ የነበሩ ጣዖታት ናቸው።) ነፍሱን ለማዳን ከሽርክ ለመፅዳትና ለዛ መሀላው ማካካሻ እንዲሆነው አስከትሎ "ላኢላሃ ኢለሏህ" የማለት ግዴታ እንዳለበት ተናገሩ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለባልደረባው "ና ቁማር እንጫወት" ያለ ሰው (ቁማር ማለት ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸው አሸናፊው የሚወስደው ገንዘብ መድበው ለመሸናነፍ መጫወት ነው። ከመካከላቸውም እያንዳንዳቸው ወይ ያተርፋል ወይ ይከፍላል።) የጠራበትን ወንጀል ለማካካስ አንዳች ነገር መመፅወቱ እንደሚወደድለት ተናገሩ።

فوائد الحديث

መሀላ በአላህ፣ በስሞቹና በባህሪያቱ ካልሆነ በቀር አይሆንም።

ከአላህ ውጪ መማል ክልክል ነው። ይህም እንደላትና ዑዛ በመሰሉ በጣዖታትም ማለ ወይም በታማኝነት ማለ ወይም በነቢዩ ማለ ወይም ከዚህ ውጪ ባሉም ቢምል ተመሳሳይ ነው።

ኸጧቢ እንዲህ ብለዋል: «መሀላ የሚፈፀመው ታላቅ ተመላኪ በሆነ ብቻ ነው። በላትና በመሳሰሉት የማለ ጊዜ ከሃዲያን ጋር ተጠጋግቷል። ስለዚህም የተውሒድን ቃል እንዲያክል ታዘዘ።»

ከአላህ ውጪ በማለ ሰው ላይ የመሀላ ማካካሻ የለበትም። ያለበት ግዴታ ተውበትና ምህረትን መጠየቅ ነው። ይህም ከተውበት ውጪ ምንም ሊያስምረው የማይችል ትልቅ ወንጀል ስለሆነ ነው።

በሁሉም ቅርፁና ይዘቱ ቁማር ክልክል መሆኑን እንረዳለን። ይህም አላህ ከአስካሪ መጠጥና ከጣዖት አምልኮ ጋር አቆራኝቶ የከለከለው ቁማር ነው።

ወንጀልን ከፈፀሙ በኋላ ከወንጀሉ መመለስ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።

ኃጢዐት ላይ የወደቀ ሰው መልካም ስራን ሊያስከትልላት ይገባል። መልካም ስራዎች ኃጢአቶችን ያስወግዳሉና።

التصنيفات

የተከለከሉ ቃላቶችና የምላስ ወለምታ