አላህ ግዴታ ያደረገው ሲተገበር እንደሚወደው፤ ያግራራውም ሲተገበር ይወዳል።

አላህ ግዴታ ያደረገው ሲተገበር እንደሚወደው፤ ያግራራውም ሲተገበር ይወዳል።

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ግዴታ ያደረገው ሲተገበር እንደሚወደው፤ ያግራራውም ሲተገበር ይወዳል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ አምልኮና ህግጋቶቹን በማቅለል የደነገጋቸው ማግራሪያዎች ሲተገበሩ እንደሚወድ ተናገሩ። እንዲሁም አቅመ አዳምና ጤነኛ የሆኑ ሰዎች በተቸገሩ ሰዓት የደነገገላቸውን ማቅለያዎች ለምሳሌ፦ ጉዞ ላይ ሰላትን ማሳጠርና ሰላትን ሰብስቦ መስገድ ይመስል ሲፈጸሙም አላህ እንደሚወድ ተናገሩ። ይህም ልክ ግዴታ ያደረጋቸው ሲሰሩ (ተግባራዊ ሲደረጉ) እንደሚወደው ነው። ምክንያቱም አላህ ባግራራውም ጉዳዮች ሆነ ግዴታ ባደረገው ጉዳዮች ላይ ትእዛዙ አንድ ነውና።

فوائد الحديث

ጥራት የተገባው አላህ የደነገጋቸው ማግራሪያዎች ሲሰሩ መውደዱ አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን እዝነት እንረዳለን።

የዚህን ሸሪዐ ምሉእነትና በሙስሊም ላይ ችግርን ያነሳ መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

ሸሪዓዊ ፍርድ, Religious Assignment and its Conditions, ሸሪዓዊ አላማዎች