ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ሁኔታቸው አላህን ያወሱ ነበር።

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ሁኔታቸው አላህን ያወሱ ነበር።

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ሁኔታቸው አላህን ያወሱ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአማኞች እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህን በማውሳት ላይ እጅግ ጉጉ እንደነበሩና በሁሉም ወቅት፣ ስፍራና ሁኔታ ላይ ሆነውም አላህን ያወሱ እንደነበር ተናገረች።

فوائد الحديث

አላህን ለማውሳት ከትንሹም ሆነ ከትልቁ ሐደሥ መፅዳት መስፈርት አይደለም።

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህን በማውሳት ላይ ዘውታሪ እንደነበሩ እንረዳለን።

መፀዳዳትን በመሰለ አላህን ማውሳት በሚከለከልባቸው ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከመከተል አኳያ በሁሉም ሁኔታ ላይ አላህን ማውሳት በማብዛት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

التصنيفات

የቁርአንና የቁርአን መፅሀፍ ህግጋት