የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ በሚታጠቡ ጊዜ ሁለት እጃቸውን ይታጠቡና ለሶላት የሚያደርጉትን አምሳያ ዉዱእ ያደርጋሉ። ከዚያም (ሙሉ…

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ በሚታጠቡ ጊዜ ሁለት እጃቸውን ይታጠቡና ለሶላት የሚያደርጉትን አምሳያ ዉዱእ ያደርጋሉ። ከዚያም (ሙሉ ገላቸውን) ይታጠቡ ነበር።

ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ በሚታጠቡ ጊዜ ሁለት እጃቸውን ይታጠቡና ለሶላት የሚያደርጉትን አምሳያ ዉዱእ ያደርጋሉ። ከዚያም (ሙሉ ገላቸውን) ይታጠቡ ነበር። ከዚያም በእጃቸው ፀጉራቸውን ይፈለፍላሉ። (የፀጉራቸው) ቆዳ በውሃ መራሱን እስከሚያስቡ ድረስም እየፈለፈሉ በጭንቅላታቸው ላይ ሶስት ጊዜ ውሃን ያፈሳሉ። ከዚያም ቀሪ ሰውነታቸውን ያጥባሉ።" ዓኢሻ እንዲህም ብላለች: "እኔና የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአንድ እቃ ሁለታችንም እየዘገንን እንታጠብ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ መታጠብን በፈለጉ ጊዜ እጃቸውን በመታጠብ ይጀምሩ ነበር። ቀጥለውም ልክ ለሶላት እንደሚያደርጉት አምሳያ ዉዱእ ያደርጉ ነበር። ቀጥለውም ውሃን በሰውነታቸው ላይ ያፈሳሉ። ቀጥለው የጭንቅላታቸውን ፀጉር በእጆቻቸው ይፈለፍላሉ። ውሃው ወደ ፀጉራቸው ስር መድረሱንና የጭንቅላታቸውን ቆዳ ማራሱን ያሰቡ ጊዜ በጭንቅላታቸው ላይ ሶስት ጊዜ ውሃን ያፈሳሉ። ቀጥለው ቀሪ ሰውነታቸውን ያጥባሉ። ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - "እኔና የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአንድ እቃ ሁለታችንም እየዘገንን እንታጠብ ነበር።" ብላለች።

فوائد الحديث

ትጥበት ሁለት አይነት ነው። እነሱም: ከግዴታ የሚያብቃቃ ትጥበትና የተሟላ ትጥበት ናቸው። ከግዴታ የሚያብቃቃው ትጥበት: ሰውዬው ጦሀራ ማድረግን ነይቶ ከመጉመጥመጥና አፍንጫ ውስጥ ውሃን ከመክተት ጋር ሰውነቱን በውሃ ማዳረሱ ነው። የተሟላው ትጥበት ደግሞ: በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደታጠቡት መታጠብ ነው።

ጀናባ የሚለው ቃል የዘር ፈሳሽ ያፈሰሰን ወይም የዘር ፈሳሽ ባያፈስ እንኳ ግንኙነት የፈፀመን ሁሉ የምትገልፅ ቃል ናት።

ባለ ትዳሮች የሆኑ አንዱ የሌላኛውን ሀፍረተ ገላ መመልከትና ከአንድ እቃ ውሃ እየወሰዱ መታጠብ እንደሚፈቀድላቸው እንረዳለን።

التصنيفات

ትጥበት