إعدادات العرض
በአላህ ድንበር ላይ በአግባቡ የቆሙና የርሱን ድንበር የሚተላለፉ ሰዎች ምሳሌ በመርከብ ላይ (ቦታ ለመምረጥ) እጣ እንደተጣጣሉ ሰዎች ምሳሌ ነው። (በእጣው መሰረት) ከፊሉን የመርከቡ…
በአላህ ድንበር ላይ በአግባቡ የቆሙና የርሱን ድንበር የሚተላለፉ ሰዎች ምሳሌ በመርከብ ላይ (ቦታ ለመምረጥ) እጣ እንደተጣጣሉ ሰዎች ምሳሌ ነው። (በእጣው መሰረት) ከፊሉን የመርከቡ የላይኛው ክፍል ሲደርሰው ከፊሉን ደግሞ የታችኛው ክፍል ደረሰው።
ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "በአላህ ድንበር ላይ በአግባቡ የቆሙና የርሱን ድንበር የሚተላለፉ ሰዎች ምሳሌ በመርከብ ላይ (ቦታ ለመምረጥ) እጣ እንደተጣጣሉ ሰዎች ምሳሌ ነው። (በእጣው መሰረት) ከፊሉን የመርከቡ የላይኛው ክፍል ሲደርሰው ከፊሉን ደግሞ የታችኛው ክፍል ደረሰው። የመርከቡ ታችኛው ክፍል ያሉት ውሃ ለመጠጣት የፈለጉ ጊዜ ላይኛው ክፍል ባሉት በኩል ያልፉ ነበርና "እኛም (ውሃ ለማግኘት) ፋንታችንን መርከቡን ብንሸነቁርና ከኛ በላይ ያሉትን ባናውካቸው መልካም ነው።" ተባባሉ። ከላይ ያሉት የታችኞቹ ፍላጎታቸውን እንዲፈፅሙ ከተዋቸው ሁሉም ይጠፋሉ። እጃቸውን ከያዙ ደግሞ እነሱም ይድናሉ። ሁሉም ይድናሉ።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල Русский Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە Tiếng Việt ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or नेपाली Malagasy Kinyarwanda తెలుగు Lietuvių Oromoo Română മലയാളം Nederlands Soomaali Српски Українська Deutsch ಕನ್ನಡ Wolof Moore Shqip ქართული Azərbaycan Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ ድንበር ላይ ለቆሙ፣ በአላህ ትእዛዝ ላይ ቀጥ ላሉ፣ በመልካም ለሚያዙና ከመጥፎ ለሚከለክሉ ሰዎች ምሳሌ አደረጉ። የአላህን ድንበር የሚተላለፉ፣ መልካምን የተዉና ውግዝን የሚተገብሩ ሰዎች በማህበረሰቡ መዳን ላይ የሚያሳድሩት አሻራ ምሳሌው በመርከብ እንደተሳፈሩ ሰዎች ምሳሌ ነው። የመርከቡ የላይኛው ክፍልና የታችኛው ክፍል የሚቀመጠውን ለመወሰን እጣ ተጣጣሉ። ከፊሉ የላይኛው ክፍል ሲደርሰው ከፊሉ ደግሞ ታችኛው ክፍል ደረሰው። ከታች በኩል ያሉት ውሃ ማምጣት የፈለጉ ጊዜ ከላያቸው ወዳሉት ያልፉ ነበር። ከታች በኩል ያሉት "ባለንበት ስፍራ ከታች ብንቀደው ኖሮ በርሱ በኩል ውሃ እናገኝ ነበር። ከላያችን ያሉትንም አናስቸግርም ነበር።" አሉ። ከላይ በኩል ያሉት ይህንን እንዲፈፅሙ ከተዋቸው ሁሉንም እንደያዘች መርከቧ ትሰምጣለች። ከዚህ ተግባራቸው ለመከልከል ቆመው ማቀብ ከቻሉ ደሞ ሁለቱም ክፍሎች ባጠቃላይ ይድናሉ።فوائد الحديث
ማህበረሰቡን ለመጠበቅና ለማዳን በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል አንገብጋቢ መሆኑን እንረዳለን።
ሀሳቡ ህዋሳዊ (በተጨባጭ ምስል ከሳች) በሆነ መልኩ ለአእምሮ ቀለል እንዲል ምሳሌዎችን መጠቀም ከማስተማር መንገዶች መካከል አንዱ ነው።
ግልፅ የሆነ ውግዝ ተግባር ያለምንም አውጋዥ መፈፀሙ ጉዳቱ ወደ ሁሉም የሚመለስ ብክለት ነው።
የማህበረሰብ ውድመት መጥፎ ሰዎች በምድር ላይ ብልሽትን ሲያሰራጩ ችላ ማለትን ተከትሎ የሚመጣ መዘዝ ነው።
የተሳሳተ እርምጃ በጥሩ ኒያም ቢሆን ስራን አያስተካክልም።
በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ያለ ተጠያቂነት የጋራ ነው እንጂ በግለሰብ ላይ ብቻ የሚወሰን አይደለም።
የውስን ሰዎች ወንጀል ካልተወገዘ ህዝቡን የሚጠቀልል ቅጣት እንደሚያስከስት እንረዳለን።
ልክ እንደሙናፊቆቹ የክፉ ስራ ባለቤቶችም መጥፎ ስራቸውን ለማህበረሰቡ ግልፅ የሚያደርጉት መልካም ስራ አስመስለው ነው።
التصنيفات
በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ደረጃ