إعدادات العرض
‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›
‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›
ከመዕዳን ቢን አቢ ጦልሐ አልየዕመሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ ነፃ ወጪ ባሪያ የነበረውን ሠውባንን አገኘሁትና እንዲህ አልኩት: አላህ በርሱ ጀነት እንድገባ የሚያደርግብኝን የምሰራውን ስራ ንገረኝ? ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ስራ ንገረኝ? እርሱም ዝም አለ። በድጋሚ ጠየቅኩት አሁንም ዝም አለ። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቅኩት እርሱም: "ስለዚህ ጉዳይ የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠየቅኳቸውና እንዲህ አሉኝ ‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›"» መዕዳን እንዲህ አለ «ቀጥሎ አቡ ደርዳእን አገኘሁና ጠየቅኩት። እርሱም ሠውባን ያለኝን አምሳያ ነገረኝ።»
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Hausa Kurdî Kiswahili Português தமிழ் دری অসমীয়া Svenska ไทย Yorùbá Кыргызча ગુજરાતી नेपाली Română മലയാളം Nederlands Oromoo తెలుగు پښتو Soomaali Kinyarwanda Malagasyالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጀነት ለመግባት ሰበብ ስለሆነ ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስለሆነ ስራ ተጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጠያቂው እንዲህ አሉት: ሶላት ውስጥ ሱጁድ ማብዛትን አዘውትር! አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም ቢምርህ እንጂ አንድም ሱጁድ ለአላህ አትወርድም።فوائد الحديث
ሶላት ሱጁድን ስለሚያካትት ግዴታም ሆነ ሱና ሶላት ለመስገድ ጥረት በማድረግ ላይ ሙስሊሞች መበረታታታቸው፤
የሶሐቦች ግንዛቤና እውቀት መገለፁ። ይህም ጀነት ከአላህ እዝነት በኋላ በስራ ካልሆነ በቀር እንደማትገኝ ማወቃቸው ነው።
ሶላት ውስጥ ሱጁድ ማድረግ ደረጃን ከፍ ለማድረግና ወንጀሎችን ለማስማር ትልቁ ምክንያት ነው።
التصنيفات
የሶላት ትሩፋት