إعدادات العرض
የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም።
የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም።
ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tagalog ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు മലയാളം ไทย Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuvių Wolof Українська ქართული Moore Magyar Shqipالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፋቲሓን ምዕራፍ በመቅራት ካልሆነ በቀር ሶላት ትክክለኛ እንደማትሆን ገለፁ። ፋቲሓ በሁሉም ረከዓዎች ከሚደረጉ የሶላት ማእዘናት መካከል አንዷ ናት።فوائد الحديث
ፋቲሓን መቅራት እየቻለ ፋቲሓን ከመቅራት ፋንታ ሌላ ምእራፍ መቅራት አያብቃቃም።
አውቆም ሆነ ሳያውቅ ወይም ረስቶ ፋቲሓ ያልተቀራበት ረከዓ የተበላሸ መሆኑን እንረዳለን። ምክንያቱም ፋቲሓ የሶላት ማእዘን ናት። ማእዘን ደግሞ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን አይወድቅም።
ተከታይ የሆነ ሰው ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ቢደርስበት ፋቲሓን የመቅራት ግዴታው ይነሳለታል።
التصنيفات
የሰላት ማዕዘናት