إعدادات العرض
እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምን ሆነው ነው? እኔ ግን እሰግዳለሁም እተኛለሁም፤ እጾማለሁም አፈጥራለሁም፤ ሴትንም አገባለሁ! ከኔ ፈለግ ውጭ የሰራ ከኔ አይደለም።
እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምን ሆነው ነው? እኔ ግን እሰግዳለሁም እተኛለሁም፤ እጾማለሁም አፈጥራለሁም፤ ሴትንም አገባለሁ! ከኔ ፈለግ ውጭ የሰራ ከኔ አይደለም።
ከአነስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የተወሰኑ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሚስቶች ስለርሳቸው ድብቅ (ቤት ውስጥ የሚሰሩት) ዒባዳ ጠየቁ። (የርሳቸውን የቤት ውስጥ ስራ ከሰሙ በኋላ) አንዱ እንዲህ አለ "እኔ ሴት አላገባም!" አንዱ ደግሞ "እኔ ስጋ አልበላም!" አለ። ሌላኛው ደግሞ "እኔ ፍራሽ ላይ አልተኛም!" አለ። እርሳቸውም አላህን ካመሰገኑና ካወደሱ በኋላ እንዲህ አሉ "እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምን ሆነው ነው? እኔ ግን እሰግዳለሁም እተኛለሁም፤ እጾማለሁም አፈጥራለሁም፤ ሴትንም አገባለሁ! ከኔ ፈለግ ውጭ የሰራ ከኔ አይደለም።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Português සිංහල Kiswahili অসমীয়া Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands Hausa മലയാളം Românăالشرح
የተወሰኑ ሶሐቦች - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቤት ውስጥ በድብቅ ስለሚሰሩት ዒባዳ ለመጠየቅ ወደ ሚስቶቻቸው ቤት መጡ። የርሳቸው የቤት ውስጥ አምልኮ ሲነገራቸውም የራሳቸውን ስራ አሳንሰው ተመለከቱና እንዲህ አሉ: "እኛ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንፃር የት ነን? ለርሳቸው ያሳለፉትንም ሆነ የሚመጣውን ወንጀል ተምረዋል። እኛስ ከርሳቸው ተቃራኒ ምህረት ማግኘታችንን እንኳ አላወቅንም። ስለዚህ ይህን የአላህ ምህረት ለማግኘት አምልኳችን ከገደብ ያለፈ መሆን አለበት።" ቀጥለውም አንዱ "እኔ ሴት አላገባም!" አለ። ሁለተኛው ደግሞ "እኔ ስጋ አልበላም!" አለ። ሌላኛው ደግሞ "እኔ ፍራሽ ላይ አልተኛም።" አለ። ይህ ንግግራቸውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘንድ ደረሰና ተቆጡ። ለሰዎችም ኹጥባ አደረጉ። አላህን አመስግነው ካወደሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምንድነው ጉዳያቸው? ወላሂ እኔ ከሁላቹም እጅግ አላህን ፈሪውና ተጠንቃቂው ነኝ። ነገር ግን እኔ ሌሊት ለመቆም እንድበራታ እተኛለሁ፤ ለጾም እንድበራታም አፈጥራለሁ፤ ሴትንም አገባለሁ። ከኔ መንገድ አፈንግጦ ከኔ መንገድ ውጪ የተሟላ መንገድ እንዳለ የተመለከተና ከኔ መንገድ ውጪ የያዘ ሰው ከኔ አይደለም።"فوائد الحديث
ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ለመልካም ነገር ያላቸው ውዴታ፤ በመልካም ነገር ላይና ነቢያቸውን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከተል ላይ ያላቸውን ፍላጎት እንረዳለን።
የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ተግባርና መመሪያ ስንወስድ የዚህ ሸሪዓ ገርነትና ቀላልነትን እንረዳለን።
መልካም ነገርና በረካ የሚገኘው ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ተምሳሌት በማድረግና የላቀውን ባህሪያቸው በመከተል መሆኑን እንረዳለን።
የማይችለውን አምልኮ ነፍስ ላይ ማጥበቅ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም የቢድዓ ሰዎች ባህሪ ነው።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «አምልኮን አክርሮ መያዝ ከመሰረቱ እንዲቋረጥ ወደሚያደርግ መሰላቸት ያደርሰዋል። ግዴታ ነገሮች ላይ ብቻ መገደብና ትርፍ ተግባራትን መተው ደግሞ ቦዘኔነትን ወደመምረጥና ለአምልኮ ንቁ ወዳለመሆን ያደርሳል። የተሻለው ሚዛናዊ መሆን ነው።
ከዚህ ሐዲሥ ትላልቅ ሰዎችን በድርጊታቸው ለመከተል ብሎ ሁኔታቸውን ማጥናት እንደሚገባ እንረዳለን። ከወንዶች ማወቅ ካልተቻለ ከሴቶችም ማጣራት እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
ከዚህ ሐዲሥ ውስጥ ለአቅመ አዳም የደረሱ ሰዎችን መምከር፤ እውቀታዊ ነጥቦችን ማስተላለፍና ህግጋቶችን ማብራራት፤ ሸሪዓን ለመመርመር እውቀታቸው የደረሱ ሰዎችን ደግሞ ማምታቻዎችን ልናስወግድላቸው እንደሚገባ እንረዳለን።
አንድ ሙስሊም ያሉበትን ሌሎች ሐቆች በአግባቡ ያሟላ ዘንድ አምልኮ ላይ ግዴታዎችና ሱንና (ግዴታ ያልሆኑትን) ጠብቆ ከመተግበሩም ጋር ለዘብተኛ እንዲሆን መታዘዙን ተረድተናል።
ይህ ሐዲሥ የጋብቻን ትሩፋትና በጋብቻ ላይ መነሳሳቱን የሚጠቁም ሐዲሥ ነው።
التصنيفات
ነቢያዊ መመሪያ