إعدادات العرض
እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሲታጠብም ጭንቅላቱንም ገላውንም መታጠብ አለበት።
እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሲታጠብም ጭንቅላቱንም ገላውንም መታጠብ አለበት።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሲታጠብም ጭንቅላቱንም ገላውንም መታጠብ አለበት።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली മലയാളം Bosanski Italiano ಕನ್ನಡ Kurdî Oromoo Română Soomaali Shqip Српски Українська Wolof Tagalogالشرح
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ለአቅመ አዳምና የደረሰና አዕምሮው ጤነኛ በሆነ ሙስሊም ላይ ሁሉ በሳምንት ውስጥ ካሉት ሰባት ቀናት አንዱን ቀን የመታጠብ የጠበቀ ሀቅ እንዳለበት ተናገሩ። በዚህ ቀንም ንፅህናንና ፅዳትን በመፈለግ ጭንቅላቱንና ሰውነቱን ይታጠባል። ይህንን ሀሳብ ከሚያንፀባርቁ አንዳንድ ዘገባዎች እንደምንረዳው ከነዚህ ቀናቶች ሁሉ ለመታጠብ በላጩ ቀን የጁሙዐ ቀን ነው። ለምሳሌ ያህል ሀሙስ ቀን እንኳ ታጥቦ የጁሙዐ ቀን ከሶላት በፊት መታጠቡ አፅንኦት የተሰጠው ተወዳጅ ጉዳይ ነው። የጁሙዐ ቀን መታጠብን ከግዴታነት የሚያዞረው (ግዴታ አለመሆኑን የሚያሳየው) የእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና እንዲህ የሚለው ንግግር ነው "ሰዎች ነፍሶቻቸውን ለመቀለብ የሚሰሩ ነበሩ። ወደ ጁሙዐ የመጡ ጊዜም በዛው በስራ ድባባቸው ይመጡ ነበር። ለነርሱም 'ብትታጠቡስ' ተባሉ።" (ቡኻሪ ዘግበውታል) በሌላ ዘገባቸው "እየሸተቱም ይመጡ ነበር።" ማለትም የላብና የመሳሰሉት ሽታ እየሸተቱ ይመጡ ነበር። ከዚህ ሁኔታቸው ጋርም ሆነው "ብትታጠቡስ" መባላቸው ከነርሱ ውጪ ያለው ግዴታው ላይሆን ይበልጥ የተገባ ነው።فوائد الحديث
ኢስላም ለንፅህናና ፅዳት ትኩረትና ቦታ መስጠቱን እንረዳለን።
የጁሙዐ ቀን ለሶላቱ ብሎ መታጠብ አፅንኦት የተሰጠው ተወዳጅ ጉዳይ ነው።
ገላን መታጠብ ሲባል ጭንቅላትም አብሮ ቢካተትም፤ ለብቻው የተጠቀሰው ትኩረት እንዲሰጠው ነው።
ሰዎች በሚታወኩበት መልኩ መጥፎ ጠረን ያለበት ሰው የመታጠብ ግዴታ አለበት።
ከመታጠቢያ ቀናቶች ሁሉ ተወዳጅነቱ የጠነከረ የሆነው ቀን ጁሙዐ ነው። ይህም ቀኑ ብልጫ ስላለው ነው።