إعدادات العرض
ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለሁ እኔ ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ጋር ለመመሳሰል እጅግ የቀረበውን ሶላት የምሰግድ ነኝ። ዱንያን እስኪለያዩ…
ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለሁ እኔ ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ጋር ለመመሳሰል እጅግ የቀረበውን ሶላት የምሰግድ ነኝ። ዱንያን እስኪለያዩ ድረስ ይህቺው ነበረች አሰጋገዳቸው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: አቡ ሁረይራ ግዴታ ሶላቶችም ሆኑ ሱና ሶላቶች በረመዳን ውስጥም ሆነ በሌላ ወቅት በሁሉም ሶላቶች ሲሰግድ ተክቢራ ያደርግ ነበር። በሚቆም ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም ሩኩዕ በሚያደርግ ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" "አላህ ላመሰገነው ሰው ሰሚ ነው።" ይላል፤ ከዚያም ሱጁድ ከመውረዱ በፊትም "ረበና ወለከል ሐምድ" "ጌታችን ላንተ ምስጋና የተገባ ነው።" ይላል፤ ከዚያም ወደ ሱጁድ በሚወርድ ጊዜም "አሏሁ አክበር" ይላል፤ ከዚያም ራሱን ከሱጁድ በሚያነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም መልሶ ወደ ሱጁድ በሚወርድ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም መልሶ ራሱን ከሱጁድ በሚያነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም ከሁለተኛው ረከዐ መቀመጥ በኃላ በሚነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል። ሶላቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ በየሁሉም ረከዐ ይህንን ይፈፅማል። ከዚያም በጨረሰ ጊዜ እንዲህ ይላል: " ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለሁ እኔ ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ጋር ለመመሳሰል እጅግ የቀረበውን ሶላት የምሰግድ ነኝ። ዱንያን እስኪለያዩ ድረስ ይህቺው ነበረች አሰጋገዳቸው።"
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली తెలుగు Bosanski Italiano ಕನ್ನಡ Kurdî മലയാളം Oromoo Română Soomaali Shqip Српски Українська Wolof Moore Tagalogالشرح
አቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አሰጋገድ ባህሪ ከፊሉን ተናገሩ። እርሳቸው ወደ ሶላት የቆሙ ጊዜ ተክቢረተል ኢሕራም እንደሚያደርጉ፤ ቀጥለው ወደ ሩኩዕ በሚሸጋገሩ ጊዜ፣ ሱጁድ በሚያደርጉ ጊዜ፣ ከሱጁድ ራሳቸውን በሚያነሱ ጊዜ፣ ሁለተኛውን ሱጁድ በሚወርዱ ጊዜ፣ ከርሱም ራሳቸውን ቀና በሚያደርጉበት ጊዜ፣ ባለሶስት ወይም ባለአራት ረከዓ ሶላት ውስጥ ለመጀመሪያው ተሸሁድ ከተቀመጡ በኋላ ከሁለተኛው ረከዓ ሲነሱም ተክቢራ እንደሚያደርጉ፤ ቀጥለውም ሶላቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በሁሉም የሶላቱ ክፍል ይህንን ይፈፅሙ እንደነበር ተናገሩ። ወገባቸውን ከሩኩዕ በሚያነሱ ጊዜም "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" ይሉ ነበር። ከዚያም ከቆሙ በኋላ "ረበና ለከል ሐምድ" ይሉ እንደነበርም ተናገሩ። ከዚያም አቡ ሁረይራ ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ እንዲህ አሉ: ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እኔ የአላህ መልዕክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በማመሳሰል ከናንተ እጅግ የቀረብኩኝ ነኝ። ይህቺን አለም እስከሚለያዩ ድረስም የአሰጋገዳቸው ባህሪ ይህቺው ነበረች።فوائد الحديث
ከሩኩዕ በሚነሱነት ጊዜ ካልሆነ በቀር በየሁሉም መነሳትና መውረድ መካከል ተክቢራ እንደሚደረግ እንረዳለን። ከሩኩዕ ሲነሱ ግን "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" ነው የሚባለው።
ሶሐቦች ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተልና ሱናቸውን በመጠበቅ ላይ ያላቸውን ጉጉት እንረዳለን።
التصنيفات
የሶላት አሰጋገድ