إعدادات العرض
(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።
(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።
ከቡረይዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።"
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português Nederlands Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી Kiswahili پښتو ไทยالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአደራ ከመማል ከለከሉም አስጠነቀቁም። ይህን ድርጊት የፈፀመም ከኛ አይደለም አሉ።فوائد الحديث
ከአላህ ውጪ መማል ክልክል መሆኑን እንረዳለን። ከዚህም መካከል በአደራ መማል አንዱ ነው። ይህም ከትንሹ ሺርክ መካከል ነው።
አማና የምትለዋ ቃል ትእዛዝን፣ አምልኮን፣ አደራን፣ ገንዘብንና ደህንነትን የሚጠቀልል የወል ስም ነው።
መሃላ በአላህ ወይም ከስሞቹ መካከል በአንድ ስሙ ወይም ከባህሪያቶቹ መካከል በአንድ ባህሪው ካልሆነ በቀር አይታሰርም።
ኸጧቢይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ክልከላ የመጣው እርሳቸው በአላህና በባህሪያቱ እንዲምል ስላዘዙ ይመስላል። አደራ ደሞ ከአላህ ባህሪያቶች መካከል ሳይሆን ከትእዛዞቹ መካከል አንድ ትእዛዙ፣ ከግዴታዎቹ መካከል አንዱ ግዴታው ነው። ከዚህ የተከለከሉትም በርሷ መካከልና በአላህ ስምና ባህሪያት መካከል እኩል ማድረግ ስለሚሆን ነው።"
التصنيفات
ማጋራት (ሺርክ)