ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት።

ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት።

ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚንበር ላይ ሳሉ ስለ ምፅዋት፣ ጥብቅነትና ልመና ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት። ከላይ ያለች እጅ ሰጪዋ ስትሆን ከታች ደግሞ ጠያቂዋ እጅ ናት።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚንበር ላይ ኹጥባ እያደረጉ ሳሉ ስለ ምፅዋት፣ ጥብቅነትና ልመና ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "የምትሰጥ የሆነች ከላይ ያለች እጅ የምትለምን ከሆነች ከታች ካለች እጅ አላህ ዘንድ የተሻለችና ተወዳጅ ናት።"

فوائد الحديث

ከዚህ ሐዲሥ ለመልካም መንገዶች የመስጠትና የመመፅወትን ትሩፋትና የመለመንን አስከፊነት እንረዳለን።

በዚህ ሐዲሥ ከልመና መጠበቅ፣ ከሰዎች መብቃቃት፣ ከፍ ያሉ ነገሮችን እንድንላበስና የወረደን ነገር እንድንተው ተበረታቷል። አላህ ከፍ ያሉ ነገሮችን ይወዳል።

እጆች አራት አይነት ናቸው። በደረጃም የሚበላለጡት እንደሚከተለው ነው: ከፍተኛዋ ሰጪ ናት። ቀጥሎ ከመቀበል የተብቃቃች እጅ ናት። ቀጥሎ ሳትለምን የምትቀበል እጅ ናት። ቀጥሎ የመጨረሻዋ የምትለምን እጅ ናት።

التصنيفات

የፈቃደኝነት ምፅዋት (ሶደቃ), ቀለብ