ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋ ድረስ ምሽቱን የተኛ ሰውዬ ተወሳ። እርሳቸውም "ይህ ሸይጧን ጆሮዎቹ ውስጥ ወይም ጆሮው…

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋ ድረስ ምሽቱን የተኛ ሰውዬ ተወሳ። እርሳቸውም "ይህ ሸይጧን ጆሮዎቹ ውስጥ ወይም ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው።" አሉ።

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋ ድረስ ምሽቱን የተኛ ሰውዬ ተወሳ። እርሳቸውም "ይህ ሸይጧን ጆሮዎቹ ውስጥ ወይም ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው።" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋና ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ የተኛ፤ ግዴታ ሶላትን ለመስገድም ስላልተነሳ ሰውዬ ተወሳ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህ ሸይጧን ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው አሉ።

فوائد الحديث

የሌሊት ሶላት መቆምን መተው እንደሚጠላና ይህም በሸይጧን አማካይነት እንደሚሆን ተረድተናል።

በርሱና አላህን በመታዘዝ መካከል እንቅፋት ለመሆን በሁሉም መንገድ ላይ የሰውን ልጅ ለመከልከል ከሚቀመጠው ሸይጧን መጠንቀቅ እንደሚገባ ተረድተናል።

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: (ወደ ሶላት ያልቆመ) በሚለው የተፈለገው ማንኛውም የሶላት አይነትም ሊሆን ይችላል፤ ተለይቶ የታወቀን ሶላት ሊሆንም ይችላል፤ የለይል ሶላትም ሊሆን ይችላል፤ የግዴታ ሶላትም ሊሆን ይችላል።

ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: «ቦታው ላይ ለመጥቀስ ከእንቅልፍ ጋር አብሮ የሚሄደው አካል አይን ከመሆኑም ጋር ጆሮን ለይተው የጠቀሱት የእንቅልፉን ክብደት ለመግለፅ ነው። መስሚያዎች መንቂያ አካላቶች ናቸውና። ሽንት የተለየበት ምክንያትም ደሞ ወደ ውስጥ ለመግባት ቀላልና ወደ ደም ስር ለመስረፅ ፈጣን ስለሆነ ነው። ይህም ከሆነ በኋላ ለሁሉም አካል መስነፍን ያወርሳል።»

التصنيفات

የሶላት ግዴታነትና የተወው ሰው ፍርድ