ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።

ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።

ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው: "ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጁሙዓን ሶላት ለመስገድ የሚመጣ ሰው ለጀናባ እንደሚታጠበው ትጥበት አምሳያ መታጠብ ለርሱ ተወዳጅ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተው ተናገሩ።

فوائد الحديث

የጁሙዓ ትጥበት አፅንዖት የተሰጠው ጉዳይ እንደሆነ፤ የጁሙዓ ቀን መታጠብ ለአማኞች ሱና እንደሆነና ወደ ሶላት በሚሄድበት ጊዜ መሆኑ በላጭ እንደሆነ እንረዳለን።

በንፅህና እና በመልካም መዓዛ ላይ መጣር ከሙስሊም ስነምግባርና ስነስርዓት መካከል ነው። ሰዎችን በሚገናኙበት ወቅትና በሚቀማመጡበት ወቅት በተለይም በጁሙዓና በጀማዓ ሶላቶች ወቅት ደግሞ ትእዛዙ አፅንዖት ይኖረዋል።

ሐዲሡ የሚመለከተው ጁሙዓ ግዴታ ለሆነባቸው ሰዎች ነው። ይህም በጁሙዓ መገኘት የሚጠበቅበት እርሱ ስለሆነ ነው።

ጁሙዓ ለሚመጣ ሰው ንፁህ መሆኑ፣ መጥፎ ጠረኖች ከሰውነቱ እስኪወገድ ድረስ መታጠብ፣ ሽቶ መቀባቱ ይወደድለታል። ዉዱእ ብቻ ካደረገም ይበቃለታል።

التصنيفات

ትጥበት, የጁሙዓ ሶላት