إعدادات العرض
ዉዱእን አሳምሮ አድርጎ ወደ ጁሙዓ በመምጣት ኹጥባን ዝም ብሎ ያዳመጠ በዚህኛው ጁሙዓና በቀጣዩ ጁሙዓ መካከል የሰራው ተጨማሪም ሶስት ቀን የሰራው ወንጀል ይማራል።
ዉዱእን አሳምሮ አድርጎ ወደ ጁሙዓ በመምጣት ኹጥባን ዝም ብሎ ያዳመጠ በዚህኛው ጁሙዓና በቀጣዩ ጁሙዓ መካከል የሰራው ተጨማሪም ሶስት ቀን የሰራው ወንጀል ይማራል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ዉዱእን አሳምሮ አድርጎ ወደ ጁሙዓ በመምጣት ኹጥባን ዝም ብሎ ያዳመጠ በዚህኛው ጁሙዓና በቀጣዩ ጁሙዓ መካከል የሰራው ተጨማሪም ሶስት ቀን የሰራው ወንጀል ይማራል። ጠጠርን የነካካ በርግጥም (የጁመዓውን ምንዳ) ውድቅ አድርጓል።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português සිංහල অসমীয়া Kiswahili Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands پښتو नेपाली മലയാളം Svenska ไทย Кыргызча Română Malagasy ಕನ್ನಡ Српски తెలుగు ქართული Mooreالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እየነገሩን ያሉት: ዉዱእን ማዕዘናቶቹን አሟልቶ፣ ሱናዎቹንና ስነስርአቶቹንም በመፈፀም አሳምሮ ካደረገ በኃላ ወደ ጁሙዓ ሶላት በመምጣት ዝም ብሎ ኹጥባውን ያዳመጠና ከዛዛታ ነገር ዝም ያለ ሰው አላህ ለርሱ የአስር ቀን ትናንሽ ወንጀሎቹን ይምረዋል። እነሱም ከሰገደው ጁሙዓ ቀን እስከሚቀጥለው ጁሙዓ ድረስና የተጨማሪ ሶስት ቀን ወንጀል ነው። ምክንያቱም መልካም ስራ አስር አምሳያውን ያስመነዳልና። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኹጥባ ላይ ለሚነገረው ተግሳፅ የልብን ትኩረት ከመንፈግ፣ በሰውነት ከመጫወት፣ ጠጠርን በመነካካትና በሌሎችም በሚጠምዱ የጨዋታ አይነቶች ከመዘናጋት አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመ በርግጥም የጁሙዓውን የተሟላ ስራ ውድቅ አድርጎታል። ውድቅ ስራ የሰራ ሰውም ከተሟላ የጁሙዓ ምንዳ ለርሱ ድርሻ የለውም።فوائد الحديث
ዉዱእን በመፈፀም ላይ፣ በተሟላ መልኩ በማሟላት ላይና የጁሙዓ ሶላትን መጠባበቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
የጁመዓ ሶላት ትሩፋትን እንረዳለን።
ለጁሙዓ ኹጥባ ዝም ማለት፣ ከጁሙዓ ኹጥባ በማውራትና በሌላም ተግባር ከመጠመድ መጠንቀቅ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
በኹጥባ መሀል ውድቅ ተግባር የሰራ ሰው ምንዳው ከመጉደሉም ጋር የጁሙዓ ሶላቱ የሚያብቃቃውና ግዴታውን የሚያነሳለት ነው።
التصنيفات
የጁመዓህ ሶላት ትሩፋት