إعدادات العرض
በሁሉም ውስጥ መልካም ነገር ቢኖርም፤ ጠንካራ ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን አላህ ዘንድ የተሻለና ይበልጥ ተወዳጅ ነው።
በሁሉም ውስጥ መልካም ነገር ቢኖርም፤ ጠንካራ ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን አላህ ዘንድ የተሻለና ይበልጥ ተወዳጅ ነው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "በሁሉም ውስጥ መልካም ነገር ቢኖርም፤ ጠንካራ ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን አላህ ዘንድ የተሻለና ይበልጥ ተወዳጅ ነው። በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ! በአላህም ታገዝ! አትስነፍ! አንዳች ነገር ሲያገኝህም ‹እንዲህ አድርጌ በነበር እንዲህ እንዲህ ይሆን ነበር።› አትበል። ይልቁንም ‹ይህ የአላህ ውሳኔ ነው። የሻውንም ፈፀመ።› በል። (እንዲህ ቢሆን ኖሮ) ማለት የሰይጣን ስራ ትከፍታለችና።'"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali മലയാളം తెలుగు ไทย Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuvių Wolof Українська ქართული Moore Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙእሚን ሁሉ ነገሩ መልካም እንደሆነ፤ ነገር ግን በኢማኑ፣ በቆራጥነቱ፣ በገንዘቡም በሌላም የኃይል ጎን ጠንካራ የሆነው ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን የበለጠ አላህ ዘንድ ምርጥና ተወዳጅ መሆኑን ገለፁ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አማኝ ለሆነ ሰው ጥራት በተገባውና ከፍ ባለው አላህ ላይ ከመመካትና ከመታገዝ ጋር ለዱንያዊም ይሁን ለአኺራዊ ጉዳዮቹ የሚጠቅመውን ሰበቦች መያዝ እንደሚገባው መከሩ። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሁለቱ ዓለም የሚጠቅሙ ነገሮችን ከመተግበር መዳከም፣ መታከትንና መሳነፍን ከለከሉ። አማኝ የሆነ ሰው በአላህ በመታገዝ በአንድ ስራ ላይ ከታገለ፣ ሰበቦችን ከያዘና ከአላህ መልካሙን ከፈለገ በኋላ ሁሉን ነገሩ ወደ አላህ ማስጠጋትና የአላህ ምርጫ የተሻለ መሆኑን ማወቅ እንጂ ሌላ ጣጣ ውስጥ መግባት የለበትም። ከዚህም በኋላ አንድ ችግር ቢያገኘው እንዲህ ማለት የለበትም: "እንዲህ ባደርግ ኖሮ እንዲህ እንዲህ ይሆን ነበር።" ""እንዲህ ባደርግ ኖሮ" ማለት የአላህን ውሳኔ በመቃወም፣ ባለፈን ነገር በመቆጨት፣ የሰይጣንን ስራ ትከፍታለች። ነገር ግን በመቀበልና በመውደድ "ይህ የአላህ ውሳኔ ነው። አላህም የፈለገውን ፈፀመ።" ይበል። የተከሰተው ነገር አላህ በፈለገው መሰረት ነው። እርሱ የፈለገውን ነገር ፈፃሚ ነው፤ የርሱን ውሳኔ መላሽ የለም፤ ፍርዱንም የሚያቅብ የለም።فوائد الحديث
ሰዎች በኢማን እንደሚበላለጡ እንረዳለን።
በስራዎች ላይ ጠንካራ መሆን እንደሚወደድ እንረዳለን። ምክንያቱም በደካማነት የማይገኙ ጥቅሞች በጥንካሬ አማካይነት ሊገኙ ይሆናልና።
የሰው ልጅ በሚጠቅመው ነገር ላይ መጓጓትና የማይጠቅመው ነገርን ደግሞ መተው ይገባዋል።
አንድ አማኝ በሁሉም ጉዳዮቹ የአላህን እገዛ መፈለጉ ግዴታ ነው። በነፍሱ ላይ ሊመካም አይገባውም።
የአላህን ውሳኔና ፍርድ ማፅደቅ ሰበቦችን ከመፈፀምና መልካምን ለመፈለግ ከመልፋት ጋር አይጋጭም።
ችግሮች በሚያጋጥሙ ወቅት በመበሳጨት መልኩ "እንዲህ ባደርግ ኖሮ" ማለት መከልከሉንና የአላህን ፍርድና ውሳኔ መቃወም ክልክል መሆኑን እንረዳለን።