إعدادات العرض
በሰዎች ውስጥ ሁለት ነገሮች አሉ፤ ክህደት ናቸው። በዘር መተቸትና በሞተ ላይ ሙሾ ማውረድ ናቸው።
በሰዎች ውስጥ ሁለት ነገሮች አሉ፤ ክህደት ናቸው። በዘር መተቸትና በሞተ ላይ ሙሾ ማውረድ ናቸው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በሰዎች ውስጥ ሁለት ነገሮች አሉ፤ ክህደት ናቸው። በዘር መተቸትና በሞተ ላይ ሙሾ ማውረድ ናቸው።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Nederlands অসমীয়া Tiếng Việt Kiswahili ગુજરાતી پښتو ไทย Română മലയാളം Deutsch Oromoo नेपालीالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሰዎች መካከል ስለሚገኙ ሁለት የከሃዲያን ስራዎችና የድንቁርና ዘመን ስነ ምግባሮች ተናገሩ። እነርሱም: የመጀመሪያው: ሰዎችን በዘራቸው መተቸት፣ ማሳነስና በዘር እነርሱ ላይ መኩራራት ነው። ሁለተኛው: በመከራ ወቅት የአላህን ውሳኔ በማማረር ድምፅን ከፍ ማድረግ ወይም ከትእግስት ማጣት ብዛት ልብስን መቅደድ ነው።فوائد الحديث
በመተናነስ ላይና በሰዎች ላይ አለመኩራት መነሳሳቱን እንረዳለን።
በመከራ ላይ መታገስና አለመበሳጨት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
እነዚህ ተግባራት ከትንሹ ክህደት ነው የሚመደቡት። ከትንሹ ክህደት ክፍሎች መካከል አንድ ስራን የሰራ ሰው ደሞ ትልቁን ክህደት እስኪሰራ ድረስ ከእስልምና የሚያስወጣ ክህደትን የካደ አይሆንም።
እስልምና ዘር መተቻቸትና የመሳሰሉትን በሙስሊሞች መካከል መከፋፈልን የሚፈጥሩ ነገሮችን ሁሉ ከልክሏል።
التصنيفات
ክህደት (ኩፍር)