ቁርኣን የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አርባ ዓመታቸው ላይ ሳሉ ወረደ

ቁርኣን የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አርባ ዓመታቸው ላይ ሳሉ ወረደ

ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብለዋል፦ ቁርኣን የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አርባ ዓመታቸው ላይ ሳሉ ወረደ። በመካ አስራ ሦስት ዓመታት ቆዩ። ከዚያም በስደት ታዘዙ። ወደ መዲና ተሰደውም አስር ዓመታትን ቆዩ። ከዚያም ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አረፉ።

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ወሕይ (መለኮታዊ ራዕይ) በአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ የወረደውና የተላኩበት ዕድሜ አርባ መሆኑን፤ ከወሕይ መውረድ በኋላም በመካ አስራ ሶስት አመት መቆየታቸውን፤ ከዚያም ወደ መዲና እንዲሰደዱ እንደታዘዙና በመዲናም አስር አመታት እንደቆዩ፤ ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በስልሳ ሶስት አመታቸው እንዳረፉ ተናገሩ።

فوائد الحديث

ሰሓቦች ለነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ታሪክ ትኩረት መስጠታቸውን እንረዳለን።

التصنيفات

ነቢያችን ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና, የነቢዩ ታሪክ