ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከናንተ መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ አምሳያ የሚያህል ቢመፀውት የአንዳቸውንም እፍኝ ሆነ የእፍኙን ግማሽ የመፀወቱት ጋር አይደርስም።

ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከናንተ መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ አምሳያ የሚያህል ቢመፀውት የአንዳቸውንም እፍኝ ሆነ የእፍኙን ግማሽ የመፀወቱት ጋር አይደርስም።

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከናንተ መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ አምሳያ የሚያህል ቢመፀውት የአንዳቸውንም እፍኝ ሆነ የእፍኙን ግማሽ የመፀወቱት ጋር አይደርስም።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦችን ከመሳደብ ከለከሉ። በተለይ የመጀመሪያ ቀዳሚ የሆኑትን ሙሃጂሮችና አንሷሮችን መሳደብን ከለከሉ። ከሰዎች መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ የሚያህል ወርቅ ቢመፀውት የሚያገኘው ምንዳ አንድ ሶሐባ አንድ እፍኝ እህል ‐እፍኝ የተባለው መካከለኛ ሰው በሁለት እጆቹ የሚዘግነው መጠን ነው።‐ ወይም የእፍኙን ግማሽ እህል ቢመፀውት የሚያገኘው ምንዳ ጋር እኩል እንደማይሆን ተናገሩ። ይህም ከፍተኛ ኢኽላስ ስላላቸው፣ መካ ከመከፈቱ በፊት መመፅወት እጅግ አስፈላጊ በሆነበት በዛ ወቅት በመመፅወታቸውና በመዋጋታቸው ስለቀደሙ ነው።

فوائد الحديث

ሶሐቦችን (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ‐ መሳደብ ክልክልና ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል እንደሚመደብ እንረዳለን።

التصنيفات

በሶሐቦች (ረዺየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ዙሪያ የሚገባው እምነት