ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።

ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።

ከእናትችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሰጋጅ ነፍስ የሚጓጓውና ልቡ የተንጠለጠለበት ምግብ ቀርቦ መስገድን ከለከሉ። ልክ እንደዚሁ በቆሻሻው ግፊት ስለሚጠመድም ሁለቱ ቆሻሾች እያጨናነቁት (እነርሱም ሽንትና አይነ ምድር ናቸው።) ከመስገድ ከለከሉ።

فوائد الحديث

አንድ ሰጋጅ ወደ ሶላት ከመግባቱ በፊት ከሶላቱ የሚያዘናጋውን ነገር ባጠቃላይ ማራቅ ይገባዋል።

التصنيفات

የሰጋጆች ስህተት