إعدادات العرض
የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም።
የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም።
ከሱሀይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም። ደስታ በሚያጋጥመው ጊዜ ያመሰግንና ለርሱ መልካም ይሆንለታል። ጉዳት በሚያጋጥመውም ጊዜ ይታገስና ለርሱ መልካም ይሆንለታል።"»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල دری অসমীয়া ไทย Tiếng Việt Svenska Yorùbá Кыргызча ગુજરાતી नेपाली Oromoo മലയാളം Română Nederlands Soomaali پښتو తెలుగు Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Malagasy Српски Mooreالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አድናቆታዊ በሆነ መልኩ በአማኝ ጉዳይና ሁኔታ ይገረማሉ። ይህም የአማኝ ሁኔታዎች ባጠቃላይ መልካም በመሆናቸው ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ አይሆንም። አማኝ የሆነ ሰው ደስታ በሚያጋጥመው ጊዜ በርሱ ላይ አላህን ያመሰግናል። በማመስገኑም ምንዳን ያገኛል። ጉዳት ሲያጋጥመው ደግሞ ይታገሳልም አላህ ዘንድ ምንዳ አገኝበታለሁ ብሎም ያስባል። በትእግሰቱም ምንዳን ያገኛል። ስለዚህ እርሱ በሁሉም ሁኔታዎቹ በምንዳ ላይ ነው።فوائد الحديث
በደስታ ወቅት ማመስገንና በጉዳት ወቅት መታገስ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን። ይህንን የፈፀመም በሁለቱም ሀገሮች መልካምን ያገኛል። በፀጋዎች ላይ ያላመሰገነና በመከራዎች ላይ ያልታገሰ ሰው ምንዳም ያመልጠዋል ወንጀልም ይኖርበታል።
የኢማንን ደረጃ እንረዳለን። በየትኛውም ሁኔታ ምንዳ ማግኘት ለኢማን ባለቤቶች ካልሆነ በቀር ለማንም አይሆንም።
በደስታ ወቅት ማመስገንና በጉዳት ወቅት መታገስ ከአማኞች መገለጫ መካከል አንዱ እንደሆነ እንረዳለን።
በአላህ ውሳኔና ፍርድ ማመን አማኝን በሁሉም ሁኔታዎቹ ላይ የተሟላ ውዴታ እንዲኖረው ያደርገዋል። ይህም ከአማኝ ውጪ ካለ ሰው በተቃራኒው ነው። አማኝ ያልሆነ ሰው ጉዳት በሚያጋጥመው ወቅት ዘውታሪ ብስጭት ላይ ይሆናል። ከአላህ የሆኑ ፀጋዎች ባገኘ ወቅትም በፀጋው አላህን በሚወደው ላይ ቀርቶ ጭራሽ አሏህን ለማመፅ ይጠቀምበታል።
التصنيفات
ነፍስን ማጥራት