إعدادات العرض
በአላህ መንገድ ሲታገሉ አቧራ የለበሱ እግሮችን እሳት ልትነካቸው አትችልም።
በአላህ መንገድ ሲታገሉ አቧራ የለበሱ እግሮችን እሳት ልትነካቸው አትችልም።
ከአቢ ዐብስ ዐብዱራሕማን ቢን ጀብር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በአላህ መንገድ ሲታገሉ አቧራ የለበሱ እግሮችን እሳት ልትነካቸው አትችልም።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල ئۇيغۇرچە Kurdî Kiswahili Português Nederlands Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી پښتو Hausa ไทย മലയാളം नेपालीالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአላህ መንገድ እየታገለ እግሮቹን አቧራ የነካው ሰው እሳት እንደማትነካው አበሰሩ።فوائد الحديث
በአላህ መንገድ የሚታገል ሰው ከእሳት እንደዳነ መበሰሩን እንረዳለን።
አቧራው ሰውነትን ባጠቃላይ የሚያዳርስ ከመሆኑም ጋር እግር ተለይቶ የተወሳበት ምክንያት በዛ ዘመን የነበሩት አብዛኛዎቹ ሙጃሂዶች እግረኞች ስለነበሩና በማንኛውም ሁኔታ እግርን አቧራ መንካቱ የማይቀር ስለሆነ ነው።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «አቧራ እግርን መንካቱ ብቻ እሳትን እርም የሚያደርግላት ከሆነ የለፋ፣ አቅሙን የሰጠና በሙሉ ችሎታው የታገለ ሰውስ እንዴት ሊመነዳ ይሆን?»
التصنيفات
የጂሃድ ትሩፋት