ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ህይወታቸውን እስከወሰደባት ጊዜ ድረስ የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶችን ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከርሳቸው…

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ህይወታቸውን እስከወሰደባት ጊዜ ድረስ የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶችን ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከርሳቸው ህልፈት በኋላ ባለቤቶቻቸው ኢዕቲካፍ አድርገዋል።

የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ህይወታቸውን እስከወሰደባት ጊዜ ድረስ የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶችን ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከርሳቸው ህልፈት በኋላ ባለቤቶቻቸው ኢዕቲካፍ አድርገዋል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለይለተል ቀደርን በመፈለግ በመጨረሻዎቹ የረመዳን አስር ቀናቶች ኢዕቲካፍ በማድረግ እንደሚያሳልፉ ይህንንም አላህ ሩሓቸውን እስከወሰደበት ጊዜ ድረስ እንደቀጠሉበትና ከርሳቸው በኋላም ሚስቶቻቸው (ረዺየሏሁ ዐንሁነ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ኢዕቲካፍ ማድረጉን እንደቀጠሉበት ተናገረች።

فوائد الحديث

መስጂዶች ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ ለሴቶች እንኳን ሳይቀር የሸሪዓ ደንቦችን ካሟላች የተደነገገ ጉዳይ ነው። ይህ ግን ፈተና የማይገጥም ከሆነ ነው።

በረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ላይ ኢዕቲካፍ ማድረግ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አዘውትረው ስለሰሩት አፅንኦት የተሰጠው አምልኮ ነው።

ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በኋላ ሚስቶቻቸው ኢዕቲካፍ ስላደረጉ ኢዕቲካፍ ያልተሻረ ቀጣይነት ያለው ሱንና መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

ኢዕቲካፍ