መሪያችሁን ስሙ ታዘዙም! በነርሱ ላይ የተሸከሙት ግዴታ አለባቸው። በናንተም ላይ የተሸከማችሁት ግዴታ አለባችሁ።" አሉ።

መሪያችሁን ስሙ ታዘዙም! በነርሱ ላይ የተሸከሙት ግዴታ አለባቸው። በናንተም ላይ የተሸከማችሁት ግዴታ አለባችሁ።" አሉ።

ከዋኢል አልሐድረሚይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ሰለማ ቢን የዚድ አልጁዕፊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት ጠየቀ: "የአላህ ነቢይ ሆይ! ሐቃቸውን የሚጠይቁ ሐቃችንን ደግሞ የሚከለክሉን መሪዎች በኛ መካከል ቢመጡ ምን ያዙናል እስኪ ንገሩን?" እርሳቸውም ከርሱ ዘወር አሉ። እርሱም ድጋሚ ጠየቃቸው እርሳቸው ግን አሁንም ከርሱ ዘወር አሉ። እርሱም በድጋሚ ለሁለተኛ ወይም ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቃቸው። በዚህ ጊዜ አሽዐሥ ቢን ቀይስ ጎተተው። እርሳቸውም "መሪያችሁን ስሙ ታዘዙም! በነርሱ ላይ የተሸከሙት ግዴታ አለባቸው። በናንተም ላይ የተሸከማችሁት ግዴታ አለባችሁ።" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰዎች እንዲሰሙዋቸውና እንዲታዘዟቸው ሐቃቸውን ከሰዎች እየፈለጉ፤ በነርሱ ላይ ያለባቸውን ፍትህ ማስፈንን፣ ምርኮን ማከፋፈልን፣ ግፍን በመከላከል እኩልነት የመፍጠርን ሐቅ ግን ስለሚከለክሉ መሪዎች ከነርሱ ጋር ምን እንድናደርግ እንደሚያዙን ተጠየቁ። ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህንን ጥያቄ እንደጠሉ በሚያሳብቅ መልኩ ከርሱ ዘወር አሉ። ጠያቂው ግን ለሁለተኛና ለሶስተኛ ጊዜ ጥያቄውን ደገመላቸው። አሽዐሥ ቢን ቀይስም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ጠያቂውን ዝም ለማስባል ጎተተው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመልሱለት እንዲህ አሉ: "የመሪዎቻችሁን ንግግር ስሙ፤ ትእዛዛቸውን ታዘዙ። በነርሱም ላይ የተጣለባቸው ፍትህን የማስፈን፣ የህዝብን ሐቅ የማሟላት ኃላፊነት አለባቸው። በናንተም ላይ የተጣለባችሁ የመታዘዝ፣ ሐቃቸውን የመወጣት፣ በሚያደርሱት ግፍ ላይ የመታገስ ግዴታ አለባችሁ።

فوائد الحديث

መሪዎች የህዝባቸውን ሐቅ ባይወጡ እንኳ አላህን ዐዘ ወጀል በሚያስደስት መልኩ በማንኛውም ሁኔታ እነርሱን መስማትና መታዘዝ እንዳለብን እንረዳለን።

መሪዎች ካለባቸው ግዴታ በማጓደላቸው ሰዎችም በተመሳሳይ ያለባቸውን ግዴታ እንዲያጓድሉ ብቁ አያደርግም። ሁሉም ስለስራው ተጠያቂ፤ ባጓደለውም የሚያዝ ነው።

ሃይማኖት በመለዋወጥ ላይ የተገነባ አይደለም። ነገር ግን ልክ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ እንደመጣው ሌላኛው በተቃራኒ ያለበትን ግዴታ ቢያጓድል ራሱ እኛ ግን ግዴታ የሆነብንን መወጣት ነው።

التصنيفات

መሪ በህዝብ ላይ ያሉት መብቶች