ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።

ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአምልኮም ይሁን ለእውቀት ወይም ከዚህ ውጪ ላሉ መልካም አላማዎች በመጀመሪያው የቀን ክፍልም ሆነ በመጨረሻው የቀን ክፍል በማንኛውም ወቅት መስጂድ የመጣ ሰው በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ወይም በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ መስጂድ በመጣ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ ስፍራና መስተንግዶ እንዳዘጋጀለት አበሰሩ።

فوائد الحديث

ወደ መስጂድ የመሄድ ትሩፋትን፣ በመስጂድ ውስጥ በጀመዓ መስገድን በመጠባበቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ከመስጂዶች የሚቀር ሰው ስንትና ስንት ፀጋ፣ ደረጃ፣ ምንዳና አላህ የርሱን ቤት ላሰቡ ያዘጋጀው መስተንግዶ ያመልጠዋል!

ሰዎች ቤቶቻቸው የሚመጣን የሚያከብሩና ለርሱ ምግብ የሚያቀርቡ ከሆነ አላህም ተባረከ ወተዓላ ከፍጡራኑ የበለጠ እጅግ ቸር ነው። የርሱን ቤት ያሰበን ሰው ያከብረዋል፣ አላህ ለርሱም ትልቅና የላቀ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።

ወደ መስጂድ ማልዶም ይሁን አርፍዶ በሄደ ቁጥር ለርሱ መስተንግዶ ስለሚዘጋጅለት ወደ መስጂድ በመሄድ መደሰትና መመኘት ይገባል።

التصنيفات

የጀማዓህ ሶላት ትሩፋትና ህግጋት