إعدادات العرض
'ትልቅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ግዴታ ሶላት አጋጥሞት ዉዱኡን፣ ተመስጦውንና ሩኩዑን አሳምሮ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም፤ ከሶላቷ በፊት የነበረበትን ወንጀል ማስማሪያ ቢሆነው…
'ትልቅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ግዴታ ሶላት አጋጥሞት ዉዱኡን፣ ተመስጦውንና ሩኩዑን አሳምሮ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም፤ ከሶላቷ በፊት የነበረበትን ወንጀል ማስማሪያ ቢሆነው እንጂ፤ ይህም እድሜልኩን ነው።'
ከዑሥማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ: 'ትልቅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ግዴታ ሶላት አጋጥሞት ዉዱኡን፣ ተመስጦውንና ሩኩዑን አሳምሮ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም፤ ከሶላቷ በፊት የነበረበትን ወንጀል ማስማሪያ ቢሆነው እንጂ፤ ይህም እድሜልኩን ነው።'"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Español Hausa Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు ไทย മലയാളം Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuvių Wolof ქართული Magyar Moore Українськаالشرح
አንድም ሙስሊም የግዴታ ሶላት ወቅት የሚገባበትና ዉዱኡን አሳምሮና አሟልቶ የሚያደርግ፤ ቀጥሎም ቀልቡና አካሉ ሁሉ ወደ አላህ የዞሩና የአላህን ልቅና ያስተዋሉ በሚሆኑበት መልኩ በሶላቱ የሚመሰጥ፤ እንደ ሩኩዕ፣ ሱጁድና ሌሎችንም የመሳሰሉትን የሶላቱን ድርጊቶች የሚያሟላ አይሆንም ይህ ሶላቱ ላሳለፈው ትናንሽ ወንጀሎች ማስማሪያ ቢሆን እንጂ፤ ነገር ግን ይህ የሚሆነው ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል የሆነን አንድም ወንጀል እስካልሰራ ነው። ይህ ትሩፋትም ዘመናት በነጎዱ ቁጥር በሁሉም ሶላቶች ላይ እንደሚቀጥል ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገለፁ።فوائد الحديث
የባሪያውን ወንጀል የሚያስምረው ሶላት ዉዱኡን ያሳመረበትና የአላህን ፊት በመፈለግ በተመስጦ የሰገደው ሶላት ነው።
በአምልኮ ላይ የመዘውተር ትሩፋትን እንረዳለን። አምልኮ ትናንሽ ወንጀሎችን የሚያስምር አንዱ ሰበብ ነው።
ዉዱእን የማሳመር፣ ሶላትን የማሳመርና በሶላት ውስጥ የመመሰጥን ትሩፋት እንረዳለን።
ትናንሽ ወንጀሎች እንዲማሩ ትላልቅ ወንጀሎችን መራቅ ወሳኝ እንደሆነ እንረዳለን።
ትላልቅ ወንጀሎች በተውበት ካልሆነ በቀር አይማሩም።
التصنيفات
የሶላት ትሩፋት