إعدادات العرض
ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ አስከትሎ የሚላቸው ወይም የሚተገበራቸው የማይከስርባቸው ቃላት: ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተሕሚድ" (አልሐምዱ ሊላህ)፣ ሰላሳ…
ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ አስከትሎ የሚላቸው ወይም የሚተገበራቸው የማይከስርባቸው ቃላት: ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተሕሚድ" (አልሐምዱ ሊላህ)፣ ሰላሳ አራት ጊዜ "ተክቢራ" (አላሁ አክበር) ማለት ናቸው።
ከከዕብ ቢን ዑጅራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡ "ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ አስከትሎ የሚላቸው ወይም የሚተገበራቸው የማይከስርባቸው ቃላት: ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተሕሚድ" (አልሐምዱ ሊላህ)፣ ሰላሳ አራት ጊዜ "ተክቢራ" (አላሁ አክበር) ማለት ናቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt Hausa Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy Čeština नेपाली Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు ไทย മലയാളം Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuvių Wolof ქართული Magyar Mooreالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተናገራቸው የማይከስርበትንና የማይፀፀትበትን ዚክር ተናገሩ። እንደውም በቃላቶቹ ምንዳ የሚያገኝባቸው ናቸው። ከፊሉ ከከፊሉ በኋላ የሚባሉ ሲሆኑ ከግዴታ ሶላት በኋላ ነው የሚባሉት። እነርሱም: "ሱብሐነላህ"ን ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት። ማለትም አላህን ከሁሉም ጉድለት ማጥራት ነው። "አልሐምዱሊላህ"ን ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት ነው። ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በተሟላ ምሉዕነት መግለፅ ነው። "አላሁ አክበር"ን ሰላሳ አራት ጊዜ ማለት ነው። አላህ ከሁሉም ነገር ታላቅና የላቀ ነውና።فوائد الحديث
የ"ተስቢሕ"፣ የ"ተሕሚድ"ና የ"ተክቢር"ን ትሩፋት እንረዳለን። እነርሱም ቀሪ የሆኑ መልካም ስራዎች ናቸው።