{ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የምዕራፎችን መለያ አያውቁም ነበር።

{ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የምዕራፎችን መለያ አያውቁም ነበር።

ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብሏል፦ " {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የምዕራፎችን መለያ አያውቁም ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ ዘግበውታል።]

الشرح

የተከበረው ቁርኣን ምዕራፎች በነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ ሲወርዱ የሚጠናቀቁበትና ከሌላው ምእራፍ የሚለዩበትን መንገድ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አያውቁም ነበር። ይህ ግን {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነበር። እሷ ከወረደች በኋላ ያለፈው ምእራፍ እንደተጠናቀቀችና {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} ለአዲስ ምዕራፍ መክፈቻ እንደሆነች አወቁ በማለት ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ገለፁ።

فوائد الحديث

"ቢስሚላሂ" ከሱረቱል አንፋልና ተውባህ በስተቀር በምዕራፎች መካከል መለያ ነው።

التصنيفات

የቁርአን አወራረድና አሰባሰቡ, የቁርአን መሰብሰብ, Stops and Starts