إعدادات العرض
'ወደርሱ ሂድና አንተ ከእሳት ሰዎች ሳትሆን ከጀነት ሰዎች ነህ በለው።' አሉት ሰውየውም ታላቅ የብስራት ዜና ይዞ በድጋሚ (ወደ ሣቢት) ተመለሰ።
'ወደርሱ ሂድና አንተ ከእሳት ሰዎች ሳትሆን ከጀነት ሰዎች ነህ በለው።' አሉት ሰውየውም ታላቅ የብስራት ዜና ይዞ በድጋሚ (ወደ ሣቢት) ተመለሰ።
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሣቢት ቢን ቀይስን አጡት። አንድ ሰውዬ "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ስለርሱ ሁኔታ አጣርቼ አሳውቆታለሁ።" አለና ሣቢት ጋር ሲመጣ አንገቱን አቀርቅሮ ቤቱ ውስጥ ቁጭ ብሎ አገኘው። "ምን ሆነህ ነው?" አለው። ሣቢትም 'መጥፎ ነው' ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ድምፅ በላይ ድምፁን ከፍ ያደርግ ነበር። ስራውም ተበላሽቶ ከእሳት ባለቤቶች ሆኗል።" አለው። ሰውዬውም መጥቶ ሣቢት ምን እንዳለ ነገራቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና): " 'ወደርሱ ሂድና አንተ ከእሳት ሰዎች ሳትሆን ከጀነት ሰዎች ነህ በለው።' አሉት ሰውየውም ታላቅ የብስራት ዜና ይዞ በድጋሚ (ወደ ሣቢት) ተመለሰ።"
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Fulfulde Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली മലയാളം Bosanski Italiano ಕನ್ನಡ Kurdî Oromoo Română Shqip Soomaali Српски Wolof Українська Moore Tagalog தமிழ் Malagasy Azərbaycan فارسی ქართული 中文 Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሣቢት ቢን ቀይስን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አጡትና ስለርሱ ጠየቁ። አንድ ሰውዬም "የጠፋበትን ምክንያት ለርሶ መረጃውን አገኝሎታለሁ።" በማለት ወደርሱ ሄደ። ቤቱ ውስጥ አዝኖ አንገቱን አቀርቅሮ አገኘው። "ምን ሆነህ ነው?" ብሎ ጠየቀው። ሣቢትም ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ድምፅ በላይ ድምፁን ከፍ ያደርግ እንደነበር፤ አላህም ይህንን ያደረገ ሰው ስራው እንደተበላሸና የእሳት ባለቤት እንደሆነ በመናገሩ በርሱ ላይ የደረሰውን መጥፎ ነገር ነገረው። ሰውዬውም ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመመለስ ይህንን ነገራቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰውዬውን ወደ ሣቢት ተመልሶ ከእሳት ሰዎች እንዳልሆነ ነገር ግን ከጀነት ሰዎች እንደሆነ እንዲያበስረው አዘዙት። ይህም የሆነው የርሱ ድምፅ ከፍ ያለ መሆኑ ተፈጥሯዊ እና የነቢዩም የአንሷሮችም ኹጥባ አድራጊም ስለነበር ነው።فوائد الحديث
የሣቢት ቢን ቀይስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ እና እርሱ ከጀነት ሰዎች መሆኑንም መገለፁ።
የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሶሐቦች ላይ ያላቸው ትኩረትና በነርሱ ላይ ያላቸውን ክትትል እንረዳለን።
የሶሐቦችን (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ጥልቅ ፍራቻና ስራዎቻቸው እንዳይበላሽ ያላቸውን ስጋት እንረዳለን።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በህይወት እያሉ እሳቸውን በማናገር ዙሪያ ስርአትን መላበስ ግዴታ እንደሆነ ከሞቱ በኋላም የርሳቸው ሱና በሚሰማ ጊዜ ድምፅን ዝቅ ማድረግም ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።