ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እስልምናን መቀበል ፈልጌ መጣሁ። እሳቸውም በውሃና በቁርቁራ ቅጠል እንድታጠብ አዘዙኝ።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እስልምናን መቀበል ፈልጌ መጣሁ። እሳቸውም በውሃና በቁርቁራ ቅጠል እንድታጠብ አዘዙኝ።

ከቀይስ ቢን ዓሲም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እስልምናን መቀበል ፈልጌ መጣሁ። እሳቸውም በውሃና በቁርቁራ ቅጠል እንድታጠብ አዘዙኝ።"

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።]

الشرح

ቀይስ ቢን ዓሲም ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እስልምናን መቀበል ፈልጎ መጣ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በውሃ እና ቅጠሉን ለማንፃት በሚገለገሉበትና ጥሩ መአዛ ባለው የቁርቁራ ዛፍ ቅጠል እንዲታጠብ አዘዙት።

فوائد الحديث

ካፊር ወደ እስልምና በሚገባ ወቅት መታጠቡ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።

የእስልምና ደረጃንና ለነፍስም ሆነ ለአካልም ትኩረት መስጠቱን እንረዳለን።

ውኃ ንፁህ ከሆኑ ነገሮች ጋር መቀላቀሉ ከጠሀራነት አያስወጣውም።

ሳሙናና የመሳሰሉት ዘመን አመጣሽ የሆኑ ማፅጃዎች የቁርቁራ ቅጠልን ቦታ ይተካሉ።

التصنيفات

ትጥበትን ግዴታ የሚያደርጉ ነገሮች