إعدادات العرض
አላህ ግዴታዎችን ደነግጓል። (ባለመስራት) አታጥፏት። ድንበሮችን ወስኗል። አትተላለፏት። ነገሮችን ከልክሏል አትዳፈሯት። ለናንተው በማዘን ሳይረሳው አንዳንድ ነገሮችንም ዝም…
አላህ ግዴታዎችን ደነግጓል። (ባለመስራት) አታጥፏት። ድንበሮችን ወስኗል። አትተላለፏት። ነገሮችን ከልክሏል አትዳፈሯት። ለናንተው በማዘን ሳይረሳው አንዳንድ ነገሮችንም ዝም ብሏል፤ ስለርሷ አትፈላፈሉ።
ከአቡ ሠዕለባ አልኹሸኒይ ጁርሡም ቢን ናሺር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል: "አላህ ግዴታዎችን ደነግጓል። (ባለመስራት) አታጥፏት። ድንበሮችን ወስኗል። አትተላለፏት። ነገሮችን ከልክሏል አትዳፈሯት። ለናንተው በማዘን ሳይረሳው አንዳንድ ነገሮችንም ዝም ብሏል፤ ስለርሷ አትፈላፈሉ።"
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ ไทย Deutsch پښتو অসমীয়া Shqip Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Lietuvių دری Српски тоҷикӣ Kinyarwanda Română Magyar Čeština Moore Malagasy Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ Bambara ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayuالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ በማለት ተናገሩ። አላህ ብዙ ነገሮችን ግዴታ አድርጓልም ደንግጓልም። አጥብቃችሁ ያዙት፤ በመተው ወይም በመዘናጋት እንዳታጓድሉት። አላህ እናንተን የሚያቅቡና እርሱ ከማይወደው የሚያግዷችሁን የተወሰኑ ማቀቢያዎችንና ማገጃዎችን አድርጓልና በሸሪዓ ካዘዘው አትለፉ። አላህ ውግዝ ነገሮችን ስለከለከለ አትፈፅሟትም አትቅረቧትም። ከነዚህ ውጪ ያሉን ግን ለባሮቹ በማዘን ትቷቸዋል ዝምም ብሏቸዋል። ልክ በመሰረቱ እንደነበረው ፍቁድ እንደሆነ ይቀራል። ስለርሱም አትፈላፈሉ።فوائد الحديث
ይህ ሐዲሥ አላህ ብቻ ህግ ደንጋጊ እንደሆነና ነገሮች በእጁ እንደሆኑ ይጠቁማል።
ይህ ሐዲሥ በመፍረድም ይሁን በመፍቀድ ረገድ የሸሪዓን መርሆዎች ያካተተ ሐዲሥ ነው። ምክንያቱም ሸሪዓዊ ብይን: ወይ ዝም የተባለ ነው ወይም የተዘረዘረ ነው። የተዘረዘረ የሸሪዓ ብይን ወይ በግዴታነትም ይሁን በተወዳጅነት የታዘዘ ነው፤ ወይም በእርምነት (ክልክልነት) ደረጃም ይሁን በውግዝነት የተከለከለ ነው፤ ወይም ደሞ የተፈቀደ ነው።
አላህ ግዴታ ሳያደርገው፣ ገደብ ሳያበጅለት፣ ሳይከለክለው በዝምታ ያለፈው ነገር ፍቁድ ነው።
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በዚህ ግልፅና ፍንትው ባለ መልኩ ሐዲሡን መዘርዘራቸው ውብ የሆነ የማብራራት ብቃት እንዳላቸው ያስረዳናል።
አላህ ግዴታ ያደረጋቸውን ነገሮች መጠባበቅ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
የአላህን ድንበሮች መተላለፍ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
التصنيفات
ሸሪዓዊ መቅጫ ህግ