إعدادات العرض
ለወንዶች ምርጡ የሶላት ሰልፍ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጨረሻው ነው። ለሴቶች ምርጡ ሰልፍ የመጨረሻው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጀመሪያው ነው።
ለወንዶች ምርጡ የሶላት ሰልፍ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጨረሻው ነው። ለሴቶች ምርጡ ሰልፍ የመጨረሻው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጀመሪያው ነው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ለወንዶች ምርጡ የሶላት ሰልፍ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጨረሻው ነው። ለሴቶች ምርጡ ሰልፍ የመጨረሻው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጀመሪያው ነው።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو हिन्दी 中文 Kurdî Português অসমীয়া Kiswahili ગુજરાતી Tiếng Việt Nederlands සිංහල Hausa پښتو नेपाली ไทย മലയാളം Кыргызча Malagasy Română Svenska Lietuvių తెలుగు ქართულიالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶላት ላይ ለወንዶች ምርጡ፣ በርካታ ምንዳንና ደረጃን የሚያስገኘው ሰልፍ የመጀመሪያው ሰልፍ እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ወደ ኢማሙ ስለቀረቡ፣ የርሱን ቁርአን ስለሚሰሙና ከሴቶችም ስለራቁ ነው። መጥፎው፣ ጥቂት ምንዳና ደረጃ የሚያገኘው፣ ከሸሪዓ ዓላማ የሚርቀው ሰልፍ ደግሞ የመጨረሻው ሰልፍ ነው። የሴቶች ምርጥ ሰልፍ ደግሞ የመጨረሻው ሰልፍ እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ለነሱ ሸሸግ የሚያደርጋቸው፣ ከወንዶች ጋር ከመቀላቀል፣ በነርሱ ከመታየት፣ በነርሱ ከመፈተንም የራቀ ስለሆነ ነው። መጥፎው ሰልፍ ደግሞ ከወንዶች ስለሚቀርብ፣ ለፈተና ስለምትጋለጥ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው።فوائد الحديث
ወንዶች ወደ አምልኮና ሶላት ላይ ወደ መጀመሪያው ሰልፍ እንዲቻኮሉ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ሴቶች ራሱን በቻለ ሰልፍ ከወንዶች ጋር መስጂድ ውስጥ መስገድ እንደሚፈቀድላቸው እንረዳለን። ነገር ግን ከመሸፋፈንና ከመከናነብ ጋር ነው።
ሴቶች መስጂድ ውስጥ ከተሰባሰቡ ልክ እንደ ወንዶች ሰልፍ ሰልፎች ይሰራሉ እንጂ አይበታተኑም። ይልቁንም ያለባቸው ግዴታ ልክ እንደ ወንዶቹ ሰልፍ ሶፋቸውን ማስተካል፣ ጉድለትን መሙላት ነው።
ሸሪዓ በአምልኮ ስፍራ ሳይቀር ሴቶች ከወንዶች እንዲርቁ በማነሳሳቱ (ለአለመቀላቀል) ከፍተኛ ትኩረት እንደሰጠ ግልፅ ያደርግልናል።
ሰዎች በስራቸው ልክ እንደሚበላለጡ እንረዳለን።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «የወንዶች ሰልፍ ላይ የተነገረው መልዕክት በጥቅሉ ነው የሚወሰደው። መቼም ቢሆን የወንዶች ምርጡ ሰልፍ የመጀመሪያው ነው። መጥፎው ደግሞ የመጨረሻው ነው። የሴቶች ሰልፍ ግን ሐዲሡ ላይ የተፈለገው: ከወንዶች ጋር የሚሰግዱ ሴቶችን ነው የሚመለከተው። ከወንዶች ውጪ ተለይተው ለብቻቸው ከሰገዱ ግን የነርሱም ብይን እንደወንዶቹ ነው የሚሆነው። ማለትም ምርጡ ሰልፍ የመጀመሪያው መጥፎው ደግሞ የመጨረሻው ነው የሚሆነው።»
ነወዊይ እንዲህም ብለዋል: «በሐዲሥ ውስጥ ስለሚያስገኘው ደረጃ ተወድሶ የመጣውና የተበረታታው የመጀመሪያው ሰልፍ ሰጋጁ መጀመሪያም መጣ ዘግይቶ መጣ፣ በመካከል ግርዶሽና የመሳሰሉት ቢገባም ባይገባም ኢማሙን የሚቀጥለው ሰልፍ ነው።»
التصنيفات
የጀማዓህ ሶላት ትሩፋትና ህግጋት