አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት…

አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጭንቅላቱን ከኢማሙ በፊት ቀና የሚያደርግ ሰው አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት ሊያደርግበት ወይም የሰውነት ቅርፁን የአህያ ቅርፅ ሊያደርግበት እንደሚችል በመግለፅ ከባድ ዛቻን አስተላለፉ።

فوائد الحديث

አንድ ተከታይ ከኢማሙ ጋር ያለው የመከተል ሁኔታ አራት ነው። ከአራቱ ሶስቱ የተከለከሉ ናቸው። እነርሱም: መቅደም፣ እኩል መፈፀምና ኋላ መቅረት ናቸው። ለተከታይ የተደነገገው ኢማሙን መከተል ነው።

ተከታይ የሆነ ሰው ሶላት ውስጥ ኢማሙን መከተል ግዴታው እንደሆነ እንረዳለን።

ከኢማሙ በፊት ራሱን ቀና የሚያደርግ ሰው ላይ የሰውነት ቅርፁ ወደ አህያ ቅርፅ እንደሚለወጥ የመጣው ዛቻ ሊሆን የሚችል ነገር ነው። ይህም ወደ ሌላ ፍጥረት ከመለወጥ የሚመደብ ነው።

التصنيفات

የኢማምና የተከታይ ህግጋት